2010-05-20 14:05:59

ቅዱስ አባታችን፣ ሙዚቃ/መዝሙር እና ሊጡርጊያ


ቤተ ክርስትያን በመዝሙር ወይንም በሥርዓት አምልኮ በሚቀርበው ሙዚቃ አማካኝነት የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የእግዚአብሔር መገለጥ እንደምታበሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ ከመመረጣቸው በፊት RealAudioMP3 የካቶሊክ ሥርወ እምነት ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩበት ወቅት ያቀረቡት ሰፊ ቲዮግሊያዊ እና ሥነ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ጽሑፍ እግዚአብሔርን በሥነ ጥበብ እንወድስ በሚል ርእስ ሥር ተሰባስቦ ለኅትመት መብቃቱ ተገለጠ።

ይህ በማርቺያኑም ማተሚያ ቤት ለንባብ የበቃው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጽሓፍ በማስደገፍ ጳጳሳዊ የሳሊዚያን መንበረ ጥበብ እና በኖቫራ የሙዚቃ መንበረ ጥበብ መምህር የሥነ ጥበብ ሊቅ አባ ማሲሞ ፓሎምቤላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅ. አ. ር. ገና ካርዲናል እያሉ አሁንም ቢሆን ሥነ ጥበብ ሙዚቃ እና ሊጡርጊያ በተመለከተ እንዲሁም በሥነ ጥበብ እና በሊጡርጊያ መካከል ያለው ግኑኝነት ምን እንድሚመስል የሚሰጡት ጥልቅ ሕንጸት እና ሥልጣናዊ ትምህርት፣ የቅዳሴ ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት የሚቀርቡ መዝሙሮች የሙዚቃ ሥራዎች ልክ በማንኛው የሙዚቃ መድረክ ለሚቀርበው ሙዚቃ የሚሰጠው ሥነ ውበታዊ ትኵረ እና አድናቆት ሳይሆን መንፈሳዊ ትኵረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያስተምራል። ምክንያቱም ቤተ ክርስትያን በሙዚቃው አማካኝነት ግልጸትን ነው የምትመሰክረው፣ ስለዚህ በሥነ ጥበብ ማለትም በሙዚቃ በስነ ቅብ እና ሥነ ንድፍ አማካኝነት ቤተ ክርስትያን የተገለጠው የእግዚአብሔር ታሪክ ታስተዋውቃለች፣ በቀላሉ መልእክቱን ለሁሉም ግልጽ ታደርጋለች ብለዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሥርዓተ አምልኮ ወይንም ሊጡርጊያ በማስደገፍ የሰውጠው ውሳኔ እና ይኸንን መሠረት በማድረግ፣ ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ካርዲናል በነበሩበት ወቅት እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላም የሚሰጡት መሪ ትምህርት፣ በሊጡርጊያ ወቅት ማኅበረ ክርስትያን ሊኖረው የሚገባው ባህርይ ምን እና እንዴት መሆን እንዳለበት የሚያብራራ ነው። ስለዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያጸደቀው የሥርዓት አምኮ ውሳኔ እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ስለ ሊጡርጊያ የሚሰጡት መሪ ትምህርት ሊጡርጊያውን በጥልቀት የሚያብራራ ነው የሚያክል እና የሚቀንስ በጠቅላላ የሊጡርጊያውን ሥርዓት የሚለውጥ ዓይነት ኅዳሴ አይደለም። ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ካርዲናል በነበሩበት ወቅት እና አሁን ስለ ሊጡርጊያ የሚያቀርቡት አስተምህሮ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የሚያብራራ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.