2010-05-20 14:04:22

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የግንቦት ወር የጸሎት ሃሳብ


የሰው ልጅ ለተለዩ ጸያፍ ተግባሮች መገልገያ መሣሪያ እንዲሆን እያደረገው ያለው ሕገ ወጥ ከቦታ ቦታ ሰዎች የማዘዋወሩ ኢሰብአዊ ተግባር እንዲገታ ቤተ ክርስትያን በዚህ በያዝነው ግንቦት ወር የጸሎት ሀሳብ ታደርገው ዘንድ ቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አሳስበዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚህ ኢሰብአዊ ተግባር ሴቶች እና ሕፃናት የሚገኙባቸው በጠቅላላ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመት ሕዝብ ለተለያዩ ክብር ስራዥ አመጽ እንደሚጋለጥም በማስታወስ “እኔ ግን የምጣሁት ሕይወት እንዲያገኙና የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖራቸው ነው።” ዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁ. 10 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል ማእከል በማድረግ ቤተ ክርስትያን እና ሕዝበ እግዚአብሔር በዚህ ሃሳብ ሥር ለክብር ሰራዥ ኢሰብአዊ አደጋ ለተጋለጡት እንዲጸለይ አደራ ብለዋል።

በዓለማችን ሰው ለክብር ስራዥ ኢግብረ ገብ ተግባር መሣሪያ እንዲሆን በወንጀል ቡድኖች ከተጋረጠበት አደጋ ለማላቀቅ እና ይኽ ጸያፍ ተግባር ጨርሶ እንዲወገድ ታሊታ ቁም በሚል መጠሪያ ዓለም አቀፍ የደናግሎች ጠቅላይ አለቆች ማኅበር እና ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የቤተ ክርስትያን ተቋም አነሳሽነት የተቋቋምው የግብረ ሰናይ ማኅበር አቀነባባሪ እናቴ ኤስትረያ ካስታሎነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ የግብረ ሠናይ ማኅበር በሰው ልጅ ላይ እየደረሰ ያለው ክብር ሰራዥ አመጽ ጨርሶ እንዲወገድ፣ የዓለም ማኅበርሰብ በዚህ ዓላማ ነቆት እንዲሳተፍ፣ ጸረ ሰብአዊ ተግባር በተለያዩ መድረኮች በመገኘት በማጋለጥ ላይ እንደሚገኝ አብራርተው፣ ቅዱስ አባታችን ይኽ “እኔ ግን የምጣሁት ሕይወት እንዲያገኙና የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖራቸው ነው።” የሚለውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል መርህ በማድረግ ያቀረቡት የጸሎት ሀሳብ የዚህ የግብረ ሠናይ ማኅበር መመሪያ በመሆኑም ከሳቸው የቀረበው ጥሪ እጅግ አስደስቶናል ብለዋል።

የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናቸን ያለን ክብር ተጠበቆ የመኖር መብት አለን፣ ስለዚህ ይኸንን ክብር የሚጻረር ተግባር ሁሉ ሙሉ በሙሉ መቃወም የሁላችን ኃላፊነት ነው ካሉ በኋላ፣ በተለያዩ ክብር ስራዥ ኢሰብአዊ ተግባር የተጠቁት ከወደቁበት ወጥመድ በማላቀቅ ከኅብረሰብ ጋር ተዋህደው ለመኖር እንዲችሉ ሰብአዊ መንፈሳዊ ማኅበራዊ እና ሥነ አዕምሮአዊ ሕንጸት የሚያቀርብ ማኅበር ነው ብለዋል። ይህ የዘመኑ ባርነት የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሰው ልጅ ለወሲብ አመጽ የሚያጋልጠው ተግባር መዋጋት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ገልጠው፣ በተለያዩ አገሮች ዓላማው እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ በማስታወስ፣ በደቡብ አፍሪቃ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ምክንያት በዚህች አገር ጸረ የዘመኑ ባርነት በማስደገፍ ሰፊ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑ በመግለጥ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.