2010-05-19 16:39:05

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ሮቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ 19.05.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጲጥሮስ አደባባይ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው፣ ከሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ1: “ማርያምም እንዲህ አለች። ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው በሰፊው የዛሬን ትምህርተ ክርስቶስ በጣልያንኛ ቋንቋ አቅርበዋል፣ የሚከተለውንም በእንግሊዘኛ በአጭሩ አስተምረዋል፦ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ ባለፈው ሳምንት በፖርቱጋል ያደርግሁት ሐዋርያዊ ጉብኝት የፋጢማ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ለማክበርና ልዩ የፖርቱጋላውያን የክርስትና እምነትንና የስብከተ ወንጌል ቅናትን አክብሮት ለማቅረብ አስቻለኝ። ጉብኝቱ በተረይሮ ዶ ፓኾ በሊዝቦና በመሥዋዕተ ቅዳሴ ተጅምረዋል። በመሥዋዕተ ቅዳሴ ስብከት የፖርቱጋል ክርስትያኖችን አደራ ያልኩት ትልቁን የስብከተ ወንጌል ሥራቸው አሁንም በዘመናችን እንዲያሳድሱት በማለት ነበር። የጉዞየ ዋና ምክንያት በዚሁ የእረኞች ሕጻናት ፍራንሲስኮና ጃሲንታ 10ኛ የብፅዕና ዓመት በሚዘከርበት ወቅት ወደ ፋጢማ ንግደት ለማካሄድ ነበር። በምሽቱ ያሳረግነው ጸሎተ መቍጠርያና በነጋታው የእመቤታችን ግልጸት ለማስታወስ ባሳረግነው መሥዋዕተ ቅዳሴ ማእከል ይዞ የነበረ የፋጢማ ማርያም መልእክት ላይ ያተኮረ ነበር። በመልእክቱ እመቤታችን ድንግል ማርያም ለጸሎት ለንስሐና ለለውጥ ትጠራናለች። የታሪክ ፈተናዎችና ጥቃትች በሚያሸንፈው በመሐሪው እግዚአብሔር ፍቅር ተስፋ መጣል በጌታ የድኅነት ዓላማ ማመን እንዳለብን ይጠራናል። ባደረግሁት ንግደት ስላገኘሁት ቡራኬ እያመሰገንኩ ወደ መንግሥተ ሰማይ በምናደርገው ጉዞ እንድትመራን የሁላችን ልቦች ለዘለዓለማዊ የእግዚአብሔር ምሕረት እንድትከፍትልን እንዲሁም ቤተ ክርስትያንን ለዓለም አዳኙን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በምትሰብከው ዘለዓለማዊ ተልእኮዋ እንድታጸናት የፋጢማው ድንግል ማርያምን በማደርገው ጸሎት እንድትተባበሩኝ አደራ እላለሁ።” ካሉ በኋላ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎችና ከኢጣልያ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነዋል። በመጨረሻም ለወጣቶች ሕመምትኞችና አዳዲስ ሙሽራዎችን በልዩ አስታውሰው የሚከተለውን ብለዋል። “በጰንጠቈስጠ ጸሎተ ታስዕት እንገኛለን፣ ስለሆነም እናንተን ውድ ወጣቶችን ለምእመናን በምሥጢረ ጥምቀትና በምሥጢረ ሜሮን ለሚታደለው ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ታዛዦች እንድትሆኑ አደራ እላለሁ፣ እናንተን በሕመም ለምትሳቀዩ ውድ ሕመምተኞች ችግሩን ለማሸነፍ ያስችላችሁ ዘንድ ሥቃያችሁን ለወንድማሞች መልካም እንዲሆን እንደ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር እንድታቀርቡት ያስችላችሁ ዘንድ አጽናኙን መንፈስ ቅዱስ እንድትቀበሉ አደራ እላለሁ። እናንተን አዳዲስ ሙሽሮች የምታቋቍሙት ቤተ ሰብ ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር በሆነው በመንፈስ ቅዱስ እሳት የሚመገብ ይሁንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቴን እገልጣለሁ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.