2010-05-17 13:40:08

ድጋፍ እና ቅርበት ለቅዱስ አባታችን


በኢጣሊያ የአለማውያን ምእመናን ጠቅላይ ምክር ቤት፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት አመጽ በቤተ ክርስትያን እና በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ላይ ያስከተለው ስቃይ ቤተ ክርስትያን እና ቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ለብቻቸው እንዳልሆኑ ሙሉ ትብብር፣ ድጋፍ እና ቅርበት ብሎም ተአዝዞ ለማረጋገጥ ስለ ቅዱስነታቸው እና በጠቅላላ ስለ ቤተ ቤተ ክርስትያን እንዲጸለይ ያዘጋጀው፣ የር.ሊ.ጳ. ቀን ትላትና በኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ተመርቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተፈጽመዋል።

በዚህ ለቅዱስ አባታችን ቅርበት እና የወሲብ አመጽ ሰለባ ለሆኑ ለመጸለይ በተካሄደው የጸሎት መርሃ ግብር፣ ከጠቅላላ ኢጣሊያ የተወጣጡ 200 መቶ ሺህ ምእመናን መሳተፋቸውም ተገልጠዋል። ቅዱስ አባታችን ትላትና እሁድ እኵለ ቀን ባሳረጉት የንግሥተ ሰማይ ማርያማዊ ጸሎት ለተሳተፉት እና ድጋፍ እና ቅርበት ለመሰከሩላቸው ምእመናን ከልብ የመነጨ አባታዊ ምስጋና እዳቀረቡም ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፣ ለተፈጸመው ኃጢአት ምህረት እና ይቅርታን መንጻትን እና ኃይልን ለቤተ ክርስትያን ከእግዚአብሔር በመማጠን፣ የተካሄደውን ጸሎት መርተዋል። የጸሎት መርሃ ግብር በመምራት “ለሚሰቃዩት አጽናኝ ለተናቁት ድጋፍ የሆንክ ፍጹም ኃያል እና ዘለአለማዊ እግዚአብሔር ሆይ፣ ፍትህ እና መጽናናት እንዲጎናጸፉ በንሥኃ በነጻችው ቤተ ክርስትያን ሕይወት የልጅህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገደብ የሌለው ፍቅርህን ያገኙ ዘንድ የስቃይ እረሮአቸውን አዳምጥ በማለት ጸልየዋል።

ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ንግግር ገና ር.ሊ.ጳ. እንዲሆኑ ተሹመው በጎቼን ጠብቅ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠውን ኃላፊነት በማስታወስ፣ በጎቼን ጠብቅ ማለት በጎቼን አፍቅር፣ የስቃያቸው ተካፋይ ሁን ማለት መሆኑ በማብራራት፣ በእግዚአብሔር ኃይል ይኸንን ለመፈጸም እንዲችሉና ሁሉን በማፍቀሩ ጥሪ ዘወትር እንዲታነጹ ሁሉም በጸሎት እንዲያስባቸው አደራ ብለዋል።

አንዳንድ ካህነት ለፈጸሙት የወሲብ አመጽ ሰለባ ለሆኑት ለቤተሰቦቻቸው እና ለሁሉም ካህናት የክህነት ጥሪያቸው በጸጥታ እና በፍጹም ፍቅር እና መሥዋዕት በመኖር ለሚገኙት ከተጸለየ ባኋላ፣ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስትያንን እንዲያድስ፣ በማርያም አማላጅነት አማካኝነት ሕዝበ እግዚአብሔር በር.ሊ.ጳ. ሥር ተመርተው ወንጌልን ለመመስከር ኃይል እና ብርታት እንዲያገኙ ተጸልየዋል።

ይህ ከር.ሊ.ጳ. ጋር በሚል ቃል ተመርቶ ለቅዱስ አባታችን ድጋፍ እና ትብብር የተገለጠበት የጸሎት መርሃ ግብር ምእመናን እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መካከክል ያለው የአባትነት እና የልጅነት ውኅደት የመሰከረ፣ የጸሎት መርሃ ግብር ነበር በማለት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ ቅርበት እና ትብብር የመሰከረ ብቻ ሳይሆን፣ እውነተኛ ክርስትያኖች ቤተ ክርስትያን በልጆችዋ አማካኝነት በሚፈጸመው ኃጢአት እና በዓለም የሚታየው ኃጢአት የራስዋ በማድረግ ተጸጽታ ግልጽ እና በሁሉም የሚታይ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ጋር የተጣመረ ምስክርነት ለማቅረብ ትለወጥ ዘንድ ጥሪ ያቀረበ፣ መልካም ፈቃድ የታየበት ነበር ብለዋል።

በዚህ በተካሄደው የጸሎት መርሃ ግብር የካቶሊክ ተግባር ማህበር፣ የተሃድሶ እንቅስቃሴ የንኡሳን ክርስትያን ማኅበር የኢጣሊያ የካቶሊክ ሠራተኞች ማኅበር የሚገኙባቸው የተለያዩ ብሔራዊ የካቶሊክ የአለማውያን ምእመናን ማኅበራት እና እንቅስቃሴዎች መሳተፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.