2010-05-17 15:48:25

ድህረ መግለጫ ሐዋርያዊ ጉብኝት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቱጋል፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቱጋል የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት አካሄደው ባለፈው ዓርብ አምሻቸውን ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው በሰላም መመለሳቸው የሚታወስ ነው።

ቅድስነታቸው ከፖርቶ ከተማ ሲነሱ በአጠቃላይ ሁሉም ክርስትያን ቅዱስ ወንጌል ባልደረሰበት ለማዳረስ እና ዜና ሰናዩን ለማጠነከር በመንፈስ ታድሰው አበክረው እንዲሰሩ አደራ ማለታቸው የሚታወቅ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ዑደት ያካሄዱት እኤአ በ1917 ግልጸት ቅድስት ድንግል ማርያም ያገኙ ጂያቺንታ እና ፍራንቸስኮ ብጹዓን ከተባሉ አስር ዓመታት ሲሞላቸው እንደሆነ አይዘነጋም።

ይሁን እና ቅድስነታቸው መካነ ገዳም ፋጥማ በጐበኙበት ግዜ ከምእመናን ጋር ጥልቅ የጸሎት እና አስተንትኖ ሥርዓቶች መፈጸማቸው በግማሽ ሚልዮን ህዝብ ተሸኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ መምራታቸው የፖርቱጋል ሐዋርያዊ ዑደታቸው እምብርት መኖሩ አብሮዋቸው ወደ ዚያች ሀገር የተጓዙ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን ያመልክታሉ።

በሰማየ ሰማያት ባለው ፈጣርያችን ያለንን እምነት እንድናሳድስ በዚች በምንኖርባት ዓለም በየዓለም ህዝቦች መካከል ትብብር እና ወንድማማችነት እንዲከሰት ማርያም ፋጥማን መማጸናቸው ገልጸዋል ሲሉ መገናኛ ብዙኀኑ ገልጸዋል።

ክርስትያኖች ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ልኡካነ ቅዱስ ወንጌል ናቸው እና የቅዱስ ወንጌል ምስክሮች ይሆኑ ዘንዳ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው።

የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ለሰው ዘር ድኅነት መሆኑ መገንዘብ እና መናገር የክርስትያን ሐላፊነት መሆኑ ክርስትያን ከቤተክርስትያን ጐን በመሰለፍ የዜና ሰናየ ስርጭት ተሳታፊ እንዲሆኑ በማያያዝ መግለጣቸው ይታወቃል።

ጽንስ በማስወረድ ሕይወትን መግታት ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው ሕይወትን መታደግ እንደሚገባም አበክረው ማሳሰባቸው ተነግረዋል።

በመገናኛ ብዙኀኑ መሠረት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቶ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ እዚያው ለተገኙ አንድ መቶ ሺ ምእመናን አብረን በተስፋ እንጓዝ የማንኛውም ክርስትያን ተስፋ ከከርስቶስ ጋር መነሳት ነው እና።

የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የፖርቱጋል ሐዋርያዊ ዑደት እጅግ ስኬታማ መኖሩ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኀን አስገንዝበዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስነታቸው የፖሩጋል የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት አጠቃላይ መግለጫ ሲሰጡ ፡ እንዳመለከቱት ፡ ሐዋርያዊ ዑደቱ አስደናቂ እና ቤተክርስትያን ዓቢይ ጥንካሬ ያሳየ ነበር።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቱጋል ህዝብ የተደረገላቸው ድማቅ እና ወንድማዊ አቀባበል ህዝቡ በሥርዓተ ቅዳሴዎች ያዳረገው ሱታፌ እንደተደሰቱ እና እንደረኩ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል ።

አያይዘውም የሐዋርያዊ ዑደቱ ማእከል ገዳመ ፋጥማ ቢሆንም ቅድስነታቸው ከየሀገሪቱ ጳጳሳት ከሥነ ጽሑፍ ከባህል ከኪነ ጥበብ የበላይ ተጠሪዎች ጋር ያደረጉት ግንኙነት በእጅጉ ማራኪ መኖሩ እና ምሁራን መርካታቸው አስረድተዋል።

በተለይ ቤተክርስትያን ታበስራለች ሐሳብ ታቀርባለች ትነግራለች እንጂ አታስገድድም በማለት ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ያደረጉት ስብከት ዓቢይ ተቀባይነት እና አድናቆት ማግኘቱ ቃል አቀባዩ በተጨማሪ ገልጸዋል።

ቅድስነታቸው የወቅቱ የቤተክርስትያን ስቃይ እና መከራ ከውጭ የተጣለባት ሳይሆን ቤተክርትስያኒቱ ውሰጥ በሚፈጸመው ሐጢአት መሆኑ በማስገንዘብ መቀየር ንስሐ ጸሎት እና አስተንትኖ እንደሚያስፈልግ አበክረው መግለጻቸው ያስታወሱት የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ይህንኑ ሐረግ ያነሱት ፡ ባለፉት ዓመታት እና ወራት በየቤተክርስትያን አባላት የሆኑ ውሁዳን ካህናት በሕጻናት ላይ የፈጸሙትን ቅሌት መሆኑ አስረድተዋል።

 







All the contents on this site are copyrighted ©.