2010-05-17 13:42:34

የሃይማኖት ነጻነት በምዕራቡ ዓለም


በጳጳሳዊ ላተንራነንሰ መንበረ ጥበብ የዓለም አቀፍ ሥነ ሕግ መምህር የሥነ ሕግ ሊቅ የመንበረ ጥበቡ የሕግ ተቋም ሊቀ መንበር ፕሮፈሶር ቪቸንዞ ቡኦኖሞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሃይማኖት ነጻነት RealAudioMP3 ጉዳይ እየተወሳሰበ መሆኑ በመጥቀስ፣ ይህ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ስለ ሃይማኖት በተመለከተ ካለው ግንዛቤ የመነጨ ነው። ስለዚህ የሃይማኖት ነጻነት ካለህ የሃይማኖት ግንዛቤ ጋር የተሳሰረ በውስጡ የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ ያጠቃለለ፣ በመሆኑ ለማኅበራዊ ጥቅም መሠረት ሀሳብህን የመግለጥ የማነጽ እምነትን የማስተማሩ መብት እና ፈቃድ መጠበቅ እና መከበር አለበት ብለዋል። ስለዚህ ብዙ አገሮች ከጠባብ ገጠመኝ በመነሳት ሃይማኖት ለሰላም እና ለመረጋገት መሠረት መሆኑ ከመመልከቱ ይልቅ የውጥረት እና የግጭት ምክንያት አድረገው ይመለከቱታል ይህ ደግሞ መሠረት የለሌው አመክንዮ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ነጻነት እና ሃሳብህን የመገልጥ ነጻነት ተያይዘው እንደሚሄዱም በማብራራት፣ ስለዚህ በማህበርሰብ ዘንድ መከባበር መቀባበል፣ የተሰኙት እሴቶች ማነቃቃት ወሳኝ ነው። ለምንኖርበት ዓለማም ሃይማኖት አቢይ ድጋፍ መሆኑ ገልጠው፣ የሃይማኖት ነጻነት ማጥበብ እነዚህ እሴቶች ጭምር ማግለል እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መጣስ ጭምር ያስከትላል ብለዋል። ሃይማኖት የሁሉም ሀሳብ ተቻችሎ የሚኖርበት ቅርጽ ማለት አይደለም፣ ሃይማኖት በማኅበራዊ ጉዳይ ያለው የሚሰጠው አስተዋጽኦ ችላ እየተባለ ሃይማኖት የግል ነው የሚለው አመለካከት ብዙ አገሮች ሲከተሉት ይታያል፣ ሆኖም ሃይማኖት ውጥረት ግጭት የመሳሰሉት ጸረ ሰላም ተግባሮች ለማስወገድ የሚያስችል እምቅ ኃይል እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.