2010-05-17 13:41:05

ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ቀን


የተባበሩት መንግሥታት ያነቃቃው ዓለም ዓቀፍ የቤተ ሰብ ቀን “ስደት በቤተሰብ ላይ ያለው ተጽእኖ” በሚል ርእስ ሥር ከትላንትና በስትያ ታስቦ ውሎአል። ቀኑን ምክንያት በማድረግ እዚህ በሮማ የቤተሰብ ኅብረ ብዙነት፣ የኢጣሊያ መጪው RealAudioMP3 ሕይወት ኅብረ ባህል የተረጋገጠበት ነው፣ በሚል ርእስ ሥር፣ የኢጣሊያ የቤተሰብ ጉባኤ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት የስደተኞች እና የተጓዦን ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ ባሰሙት ንግግር፣ ስደት በቤተሰብ መለያየትን መራራቅን እያስከተለ መሆኑ በማስታወስ፣ የቤተሰብ ባንድነት የመኖር መብት እና ፈቃድ በሙላት ይከበር ዘንድ አሳስበዋል። ቅዱስ አባታችን እለቱን ምክንያት በማድረግ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የስደተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በማስታወስ፣ ይኽ የኅብረሰብ ክፍል ያለበት ችግር ለመፍታት በቃት ያለው የፖሊቲካ እቅድ በዓለማችን መረጋገጥ ይኖርበታል ያሉትን ሀሳብ፣ ብፁዕነታቸው በማስታወስም፣ የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ መሠረት በዓለም ደረጃ በአገር ውስጥ ተፈናቅሎ የሚኖረው የተፈናቃይ ሕዝብ ብዛት 44 ሚሊዮን መሆኑን በመግለጥ በአገራቸው ውስጥ ያሉ በመሆናቸውም ብዙ ጊዜ ችላ እንደሚባሉ በማብራራት፣ እነዚህ የኅብረትሰብ ክፍል ድጋፍ እና ትብብር እንዳይለያቸው የሚያነቃቃ የፖለቲካ ፍቃድ እንዲኖር አደራ ብለዋል።

የኢጣልያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ለጉባኤ መልእክት ማስተላለፋቸውም ሲገለጥ፣ ቤተሰብ የውህደት መሠረት መሆኑ ባስተላለፉት መልእክት በጥልቀት በመተንተን የስደተኞች የሕፃናት የሴቶች መብት እና ፈቃድ ተረጋገጦ የስደተኞች ቤተሰብ ባንድ ጥላ ሥር ለመኖር እንዲችሉ መንግሥታት የስደተኞች መብት እና ፈቃድ በማረጋገጡ ዕድሉን እንዲፈጥሩለት ማሳሰባቸው ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.