2010-05-17 16:53:01

ባለነው ዘመን ኃጢኣትንና የዓለም ፈተናን በመቃወም እግዚአብሔርን በቍርጠኝነትና በታማኝነት ማገልግል ያስፈልጋል።


ትናንትና እሁድ ረፋድ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና በአከባቢው ያሉ ጐደናዎችን ያጥለቀለቀ ከሁለት መቶ ሺ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የንግሥተ ሰላም ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል። ምእመናኑ ከመላው ጣልያን የተሰበሰቡ ሆነው፣ ምክንያቱም በዚሁ ፈታኝ ጊዜ ምእመናን ቅዱስነታቸውን በጸሎትና በአካል እጐናቸው መሆናቸውን በማሳወቅ ድጋፋቸና አጋርነታቸውን ለመግለጥ መሆኑን ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

ቅዱስነታቸው የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ይህንን ትምህርት ሰጥተዋል፦ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ ዛሬ በዚሁ አገርና በሌሎችም አገሮች ከትንሣኤ በኋላ ከአርባ ቀናት በኋላ የተፈጸመ የጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዕርገት ይከበራል፣ ከዚህም ሌላ በዛሬው እሁድ “ካህንና የዲጂታል ግብረ ተልእኮ በዓለም፣ ኣዲስ መገናኛ ብዙኃን ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል የምናስታውሰው የመገናኛ ብዙኃን ዓለም አቀፍ ቀን ነው፣፣ ዛሬ በተነበበው የሉቃስ ወንጌል 24፣50 እና ግብረ ሐዋርያት 1፣2-9 ኢየሱስ ከሓዋርያት ተለይቶ ወደ ሰማይ ሲያርግ ስለነበረው ፍጻሜ ይተርካል፣ ይህ ዕርገት ግን መለያየት አይደለም፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ከእርሳቸውም ይሁን ከእኛ ጋራ በአዲስ መንገድ ዘወትር መሀከላችን እንደሚኖር ገልጦልናል፣ የክያራቫለ ቅዱስ በርናርዶስ የኢየሱስ ዕርገት ሶስት ደረጃዎች እንዳሉት ያመለክታል፣ የመጀመርያው የትንሣኤ ክብር ሲያመለክት ሁለተኛው ደግሞ የፍርድ ሥልጣን ሶስተኛው ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጥን ያመልክታል” ይላል። የዕርገት ፍጻሜ መንፈስ ቅዱስ በመቀበል ደኅንነትን በሁሉ ቦታ እንዲሰብኩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል እንዲዘጋጁ ለሐዋርያት በተሰጠ ቡራኬ ይመራል፣ በዚህም አጋጣሚ ኢየሱስ ለሐዋርያት “እናንተም የዚህ ሁሉ ምስክሮች ናችሁ። እነሆ እኔ የአባቴን የተስፋ ስጦታ እልክላችኋለሁ፣ እናንተም ኃይል ከላይ እስኪሰጣችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ብለዋል።

ጌታ የሐዋርያት ልብን ይሰልባል የእኛንም እንዲሁ፣ አመለካከታቸው ወደ ሰማይ እንዲያቀኑ በማመልከት በዚሁ ምድራዊ ሕይወት የበጎ አድራጎት መንገድን እንዴት ለመፈጸም እንደሚቻል ያዘጋጃል፣ እርሱ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር በመሆን የክርስትና ጉዞአችን ይመራል። ጌታ ኢየሱስ ዘወተር ከእኛ ጋር ነው፣ በሃይማኖት ምክንያት ለሚሰደዱ ጓደኛቸው፣ ለተገለሉ በልባቸው ጽናት የሚሞላ፣ የሕይወት መብታቸው ለተነጠቁ አለኝታቸው በመሆን ሁላችንን ይሸኛል። በቤተ ክርስትያን ጌታ ኢየሱስን መስማት ማየትና መንካት እንችላለን፣ በተለይ ቅዱስ ቃሉን በምንሰማበት ምሥጢራትም በሚታደሉበት ጊዜ ይህንን ማረጋገጥ እንችላለን። በዚህ የትንሣኤ ዘመን ምሥጢረ ሜሮን ለሚቀበሉ ልጆችና ወጣቶች አደራ ለማለት የምፈልገው በእግዚአብሔር ቃልና በቤተ ክርስትያን ትምህርት ጸንተው እንዲኖሩ፣ እንዲሁም ምሥጢረ ንስሐና ቅዱስ ቍርባንን እንዲያዘውትሩና እውነትን ለመመስከር እንደተመረጡ ማወቅ አለባቸው። በመጨረሻም በምሥጢረ ክህነት ወንድሞቼ ለሆኑ ካህናት “በሕይወታቸውና በተግባራቸው የጌታን ወንጌል እንዲመሰክሩ፣ እንዲሁም ምእመናን የቤተ ክርስትያን ሕይወት ለማሳወቅና የኢየሱስ ገጽታን ለማየት እንዲችሉ የብዙኃን መገናኛ መሳርያዎችን ለመጠቀም በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው” አደራ እላለሁ።

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ ጌታ የሰማይን መንገድ በመክፈት እዚህ ምድር እያለን መለኮታዊ ሕይወትን እንድናጣጥም ያደርገናል፣ ባለፈው ክፍለ ዘመን የነበረ አንድ ሩስያዊ ደራሲ “ዘወትር ከዋብትን ታዘቡ፣ ከበድበድ ያላችሁ እንደሆነም ከዋክብትንና ሰማያዊ ሰማይን ተመልከቱ፣ እንዲሁም ባዘናችሁ … ሰዎችም ሲያስቀይሙዋችሁ.. ሰማይን በማየት ተዝናኑ፣ በዚህም ሕይወታችሁ ሰላምን ታገኛለች” ብሎ ጽፈዋል።

ባለፉት ቀናት በፋጢማ መካነ ንግደት እንዳከብራት ለንግደት በሄድኩበት ወቅት ደርሼ እስክመለስ በእናታዊ ጥበቃዋ ለረዳችኝ እመቤታችን ድንግል ማርያምን አመሰግናለሁ፣ በእምነት ወደ እርስዋ እንማጠን ሲሉ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አሳርገዋል።

ከጸሎቱ በኋላ አጋርነታቸውና ቅርበታቸውን ለመግለጽ ከ200 መቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ ምእመናን በጸሎት ለመሩ ለልዑል ካርዲናል ባኛስኮና ምእመናኑን ሁሉ ልባዊ ምስጋና አቅርበው “በዓለም እንኖራለን የዓለም ግን አይደለንም፣ ከዓለም ፈተና ራሳችን መጠበቅ አለብን፣ መፍራት ያለብን ኃጢኣትን ነው፣ ለዚህም በእግዚአብሔር የተመሠረትን ለብጎ ለፍቅርና ለአገልግሎት የጸናን መሆን አለብን፣ ቤተ ክርስትያን አገልጋዮችዋና ምእመናንዋም ለዘመናት ያደረጉት ይህንን ነው፣ በእምነት ይህንን ጉዞ እንከተል” ሲሉ በመማጠን ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.