2010-05-15 14:30:52

በቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. የተመራ የመቁጸሪያ ጸሎት


15ኛው ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው በፖርቱጋል በማካሄድ ላይ የሚገኙት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛው የጉብኝታቸው ቀን በግልጸተ ማርያም ዘ ፋጢማ በሚጠራው ጸሎት ቤት ፊት በሚገኘው አደባባይ በብዙ ሺ የሚገመት ነጋድያም ምእመን ፊት የመቁጸሪያ ጸሎት በመምራት ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው።

በተካሄደው የመቁጸሪያ ጸሎት ከ 200 ሺሕ በላይ ምእመናን ፊት ቅዱስ አባታችን በዚህ በምንኖርበት ዘመን የእምነት መዛል ምክንያት የሕይወታችን ማእከል እግዚአብሔር እንዲሆን ማርያም ዘ ፋጢማ እንደምታሳስብ በመግለጥ፣ ስለ እግዚአብሔር ለመናገር እምነትን በይፋ መግለጥ የእምነት ምልክታችን ማጎላት ሊያሳፍረን አይገባም፣ ስለዚህ ካለ ማፈር ካለ ፍርሃት የምንኖረው እውነተኛው እምነት ለዘመኑ ሰው የክርስቶስ ብርኃን የሚመሰክር ይሆናል ብለዋል።

መጀመሪያ መልኣክ በመቀጠል ቅድስት ድንግል ማርያም ለሶስቱ እረኞች በመገለጥ በመቁጸሪያ ጸሎት አማካኝነት በክርስቶስ ሚሥጢራት እንድንማረክ ሚሥጢራቱን እንድናስተነትን ማሪያም በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ያላት ሱታፌ በጥልቀት እንረዳልን፣ ምንም’ኳ ስቃይ መከራ ደስታ ጨለማ እና ብርሃን በሕይወታችን ቢፈራረቅብን ሕይወታችን በክርስቶስ መሆኑ እንመሰክራለን ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.