2010-05-15 14:29:24

ማርያም ዘ ፋጢማ፣ ቀጣይ እና ቋሚ የመለወጥ ጥሪ


የሞንፎርታኒ ገዳማዊ ማኅበር አባል የሥነ ማርያም ሊቅ ኣባ ስተፋኖ ደ ፊዮረስ የማሪያም ዘ ፋጢማ መልእክት ዋናው እና መሠረታዊው ሀሳቡ ምን መሆኑ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ማርያም ቦግ ብሎ የሚጠፋው ሰው ሰራሽ መብራት ምልክት ሳትሆን ያለፈውን የምንኖርበትን እና የሚመጣው ዘመን ለመገንዘብ የሚያበቃን የማጠፋው ብርኃን የምታጎላ መሆኑ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳብራሩትም ጭምር ያብራሩት ሀሳብ መሆኑ ገልጠው፣ ማርያም በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ኃላፊነት መሆኑ የምታሳውቀ የሕይወት ባህል ከሚጻረረው ኃጢአት ለመራቅ ከንጹሕ ልበ ማርያም ጋር እራሳችንን እንድንለይ የሚጠራ መልእክት ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ቤተ ክርስትያን በአባላቷ ኃጢኣት ምክንያት በሚደርስባት በደል እና መከራ እንዲሁም በስደትን ዓመጽ በጎልጎታ የምትጓዝ መሆኗ የሚያመለክት መሆኑ በማስታወስ ቤተ ክርስትያን በመስቀል መንገድ ላይ እንዳለች የሚገልጥ ነው፣ ንገር ግን በመስቀል ተሰቅላ የምትቀር ሳትሆን ከመስቀሉ ባሻገር የላቀው ክብር ተካፋይ ለመሆን በመጓዝ ላይ እንዳለች የተረጋገጠ ነው ብለዋል። የማርያም ፋጢማ ምሥጢር ቀጣይ የሆነ ንስኃ አስፈላጊ መሆኑ እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ ለውህደት ለሰላም ለመረጋጋት መሠረት መሆኑ ያረጋገጥልናል፣ ስለዚህ የማርያም ዘ ፋጢማ መልእክት ቋሚ እና ቀጣይ የመለወጥ ጥሪ የሚያቀርብ የማርያም ንፅሕና፣ ልንሆነው የሚገባን እግዚአብሄር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያቀረበልን ጥሪ የሚመሰክር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.