2010-05-15 14:33:56

ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የድጋፍ እና የትብብር ዕለት


እ.ኤ.አ. ነገ እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢጣሊያ የዓለማውያን ምእመናን ምክር ቤት ያነቃቃው ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የድጋፍ ቀን እንደሚካሄድ ሲገለጥ፣ የተለያዩ የካቶሊክ ማኅበራት ውሉደ ክህነት የካቶሊክ አለማውያን ምእመናን እንቅስቃሴዎች እንደሚሳተፉም ተገልጠዋል።

በዚህ በሚካሄደው ለቅድስ ጴጥሮስ ተከታይ የድጋፍ ቀን የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ፣ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ሊቀ መንበር ፍራንኮ ሚያኖ ይሳተፋሉ። ሚያኖ ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው ፒውቮቸ ነጥብ ኔት በተሰኘው ድረ ገጽ በዚህ ዕለት ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ በማቅረብ ከቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በመሆን በሳቸው መሪነት ዙሪያ የጋራ ጸሎት ለማቅረብ በሳቸው በሚመራው የንግሥተ ሰማይ ማርያማዊ ጸሎት በመሳተፍ እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እና ውሉደ ክህነት ጠቅላላ የእግዚአብሄር አገልግላዮች በሁሉም ካቶሊክ ተወዳጅ መሆናቸው ለመመስከር መሆኑ እና በዚህ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን ባንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት አማካኝነት ለስቃይ በተጋለጠችበት ወቅት ለቤተ ክርስትያን መሪ የጴጥሮስ ተከታይ ቅርበት እና ፍቅር መግለጥ የሁሉም ካቶሊክ ክርትያን ኃላፊነት ነው ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.