2010-05-14 16:27:01

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት ተፈጸመ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቱጋል የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዛሬ ከቀትር በኃላ ተጠቃልለዋል።

ቅድስነታቸው በፖርቱጋል ቆያታቸው ርእሰ ከተማ ሊዝቦን ገዳመ ፋጥማ እና ፖርቶ ጐብኝተዋል።

ትናትና ከቀትር በፊት በገዳመ ፋጥማ ባካሄዱት መሥዋዕተ ቅዳሴ አምስት መቶ ሺ ህዝብ በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ መሳተፉ ታውቆዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዛሬ ጥዋት ከፋጥማ ሲነሱ የከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ጳፕሳት ካህናት እና የፋጥማ ከንቲባ እና የመንግስት ባለስልጣናት ሸኝቶዋቸዋል።

ፖርቶ ከተማ ሁለት መቶ አርባ ሺ ህዝብ የሚኖርባት ፡ ከገዳመ ፋጥማ አንድ መቶ ዘጠና ኪሎሜትር ርቃ ትገኛለች። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፖርቶ ሲገቡ

በየፖርቶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ማኑኤል ማካርዮ ዶ ናሺመንቶ ክለመንተ የሚመሩ የቤተ ክህነት አባላት የፖርቶ ከንቲባ እና የፖርቶጋል ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፖርቶ እንደገቡ አቨኒዳ ዶስ አሊዳዶስ ወደ ተባለ አደባባይ ተጉዘው በበርካታ ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ተሸንጠው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርግዋል።

በዚሁ ፖርቶ ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉበት አደባባይ በሁለት መቶ ሺ የሚገመት ህዝብ መሳተፉ ተመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባሰሙት ስብከት ፡ ከዕርገተ ክርስቶስ በኃላ ቅዱስ ጰጥሮስ ቅዱስ ጰጥሮስ የእግዚአብሔር ቃል እያነበበ እና ፍቹ እየገለጠ ኢየሱስ ክርስቶስ የተጫውተው ሚና የሚተካ እና ከኛ ጋር ሆኖ ትንሳኤው የሚመስክር ያሰፈልጋል ያለውን ጠቅሰው ፡ በርካታ ክርስቶስን ክደው ሲጠፉ የክርስቶስ ሕይወት ምስክር እና ክርስቶስ ሞትን ማሸነፉ ያየ እና የመስከረ ማትያስ መመረጡ ጠቅሰው የተወደዳችሁ ምእመናን የክርስቶስ እና የቤተክርስትያኑ ምስክሮች መሆን አለብን ብለዋል።

ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወንዝ እስከ ኢየሩሳሌም አደባባይ ክርስቶስን ለማየት እና ትምህርቱን ለማዳመጥ ህዝብ ይሰበሰብ መኖሩ ያስታወሱ ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ ትንስኤን ለማክበር የመስቀል አስፈላጊነትን ማስረዳቱ አስገንዝበዋል።

አንድ ከኛ ጋር ሆኖ የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ የሚመስክር ያስፈልጋል ያለውን ቅዱስ ጰጥሮስ አስታውሰውም ፡ የተወደድችሁ ህዝበ ክርስትያን ከኔ ጋር አብራችሁኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክት ትሆኑ ዘንዳ ልማጸናችሁ እወዳለሁኝ ብለዋል።

የቅዱስ ጰሮስ ሐዋርያ መንበር ተኪ በመሆን እዚ እናንተ ጋር ሲገኝ የሚሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው የተወዳድችሁ እኅቶቼ እና ውንድሞቼ በለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶ በፓሩጋል ፖርቶ ከተማ ላይ በሚገኘው አቨኒዳ ዶስ አልያ ዶስ አደባባይ።

ቅድስነታቸው ስብከታቸው በማያያዝ ፡አንድ ክርስትያን በቤተክርስትያን እና ከቤተክርስትያን ጋር ነው ። ክርስትያን በዓለም፡ የክርስቶስ መልእክተኛም ነው ብለዋል።

ሐቅ በክርስቶስ ከክርስቶስ ይገኛል ያሉት ቅድስነታቸው እሱ ሐቀኛ መንገድ ይመራል እሱ ሰላም እና ህያው ነው ብለዋል ።ከክርስቶስ ርቀን የምንኖር ከሆነ መኖራችን ከንቱ ውእቱ ነው። ሕይወት በክርስቶስ ይገኛል እሱ ስለወደደን ለሰው ዘር ድኅነት ሲል ያላደረገው የለም።

ምን ያህል እንደሚወደን ለማሳየት ለመግለጽ ሕይወቱ አሳልፎ እንደሰጠን መዘንጋት አይገባንም ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ።

ስለሆነም ዘወትር የክርስቶስ ትንሳኤ ምስክሮች መሆን አለብን። እሱ እኔ ሁል ግዜ እስከ መጨረሻ ዓለም ከናንተ ጋር ነኝ ብለዋል እና ብለዋል ቅድስነታቸው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በፖርቱጋል ፖርቶ ከተማ ላይ በሚገኘው አቨኒዳ ኦድስ እሊዳዶስ አደባባይ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለተገኘ በሁለት መቶ ሺ ለሚገመት ህዝብ ባሰሙት ስብከት አያይዘው እንደገለጡት ፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓለም የሥስብእና ባህላዊ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ የሰው ገጽታ መለወጡ ገልጸውም ፡ አሁን ቤተክርስትያን ለውጡ ያመጣውን ፍልሚያ በመቋቋም ከሌሎች ባህላች እና ሃይማኖቶች ጋር ለመወያየት እና ሰላማዊ የህዝቦች ኑሮ እንዲከሰት ትጥራለች በማለት ስብከታቸውን ደምድመዋል።



በዚሁ መንበረ ታቦት ዙርያ ከናንተ ጋር ለመገናኘት ስለ ፈቀደ ህያው እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የፖርቶ ጳጳስ ብፁዕ ኣአቡነ ማኑኤል ክለመንተ በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዳደርግ ላደረጉልኝ ጥሪ እና እሳቸው እና ጠቅላላ የቤተክህነት አባላት ምእመናን አማንያን ኢ አማንያን የፖርቱጋል ርእሰ ብሔር እና ህዝብ ላደረግላችሁኝ ደማቅ እና ወንድማዊ አቀባበል ከልብ በማመስገን እና ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ህዝቡን ተሰናብተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ክሥርዓተ ቅዳሴ በኃላ ወደ ፖርቶ መዘጋጃ ቤት ተጉዘው በየመዘጋጃ ቤት ሰገነት በመሆን ይጠባበቃዋቸው ለነበረ ህዝብ ሰላምታ እና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።

ከዚህ ወደ ፖርቶ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ተጉዘዋል ሲጠባበቅዋቸው ከነበሩ የሃገሪቱ የሃይማኖት እና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል ።

በሀገሪቱ ቆያቸው ለተደረገላቸው መልካም መስተንግዶ አመስግነው ከባለ ስልጣናቱ ተሰናብተው ከቀትር በኃላ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር አስራ አራት ሰዓት ላይ ከፖርቶ ተነስተው በሮማ ሰዓት አቆጣጠር አስራ ስምንት ሰዓት ላይ በሰላም ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል።

ይህ ቅዱስ አባታችን በፖርቱጋል ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሀገራት አቀፍ አስራ አምስተኛ ሐዋርያዊ ዑደት መሆኑ ይታወሳል።

ይሁን እና የፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ገዳመ ፋጥማ ማእከል ያደረገ መኖሩ የሚታወስ ሲሆን ለመጀመርያ ገዳሙ የጐበኙት ከአርባ ሶስት ዓመታት በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ነበሩ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳሎስ ዳግማዊ ሶስት ግዝያት ገዳመ ፋጥማ መጐብኘታቸው የማይዘነጋ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.