2010-05-12 14:31:23

ኢራቅ


ከትላትና በስትያ በኢራቅ ከ 110 የአገሪቱ ዜጎች ለሞት የዳረጉ የተለያዩ ጥቃቶች በባግዳድ በሞሱል በባሶራ እና በሂላ እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት መጣሉ ሲገለጥ፣ የኢራቅ የቀድሞ ቀዳሚ ሚኒ. እና በመጨረሻ RealAudioMP3 በተካሄደው ምርጫ ያሸነፉት አላዊ ይህ የተጣለው ጥቃት ሁሉም በአገሪቱ ያሉት የፖለቲካ ሰልፎች የአንድነት መንግሥት በመደገፍ ተጀምሮ የነበረው ለኢራቅ የሰላም ግንባታ ሂደት ይሰጡት የነበረው አቢይ አስተዋጽኦ ወደ ጎን በማድረግ በኢራን ተደግፈው ወጋኝ ፖለቲካ እየተከተሉ መሆናቸው የሚያረጋገጥ ነው በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

በኢራቅ የነበረው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ለመጣል የዓለም መንግሥታት በስፋት በመተባበር የደገፉት ዓላማ እግብር ላይ ከዋለ ባኋላ፣ በኢራቅ ሰላም እና መርጋጋት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ግን ታዛቢዎች እየሆኑ መምጣታቸው፣ በክልሉ ያለው ውጥረት እንደሚመሰክረው የሰላመ ክርስቶስ ማህበር የኢራቅ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ አባ ሬናቶ ሳካ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ በኢራቅ ኅብረ ሃይማኖት ኅብረ ጎሳ እና ኅብረ ፖለቲካ በሰላም የሚኖርባት አገር የማድረጉ ጥረት ሳይሳካ ቢቀር በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው አያጠራጥርም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.