2010-05-12 14:27:32

አለ እግዚአብሔር ሰላም፣ ፍትሕ እና ፍቅር ዘበት


በፖርቱጋል የማርያም ዘፋጢማ ቅዱስ ሥፍራ አስተዳዳሪ ኣባ ቪርጂሊዮ ዶ ናሺመንቶ አንቱነስ እ.ኤ.አ. ነገ ግንቦት 13 ቀን አመታዊ በአል ማርያም ዘፋጢማ ምክንያት በማርያም ዘፋጢማ ቅዱስ ሥፍራ በመገኘት የበዓሉ የቅዳሴ RealAudioMP3 ሥነ ሥርዓት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚመራ በማስታወስ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በአሁኑ ወቅት ለምንኖርበት ኅብረሰብ ምን መልእክት ታስተላልፋቸው ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም መልእክት፣ እግዚአብሔርን ማእከል ያደረገ፣ ስለ እግዚአብሔር የሚናገር የእግዚአብሔር ኅልውና የሚመሰክር ነው፣ ጸረ እግዚአብሔር አስተሳሰብ እና እግዚአብሔር የለም የሚል ርእዮተ ይስፋፋበት በነበረበት በ20ኛ ክፍለ ዘመን ነበር ማርያም በፋጢማ የተገለጸችው፣ ስለዚህ የማርያም በፋጢማ መገለጥ አለ እግዚአብሔር ሰላም ፍትሕ እና ፍቅር የጸናበት ኅብረትሰብ መገንባት ዘበት መሆኑ የሚያረጋገጥ፣ የእግዚአብሔር ኅላዌ በመመስከር ሰላም ፍትሕ እና ፍቅርን ለማጽናት የሚያችሉ መንገዶች ደግሞ ንስኃ እና ሰላም በልባችን ዘንድ እንዲነግሥ የሚያደርጉ ጸሎት እና የመቁጸርያ ጸሎት መሆናቸው የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የካቶሊክ ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩበት ወቅት፣ የማርያም በፋጢማ መገለጥ ስነ ቲዮሎጊያዊ ትንታኔ ሰጥተውበት እንደነበር የሚዝከከር ሲሆን፣ ይህ ቲዮሎጊያዊ ሰነድ፣ ሥነ ዮሓንስ ራእይ ቅርጽ እና ይዞታ ያለው፣ እርሱም የታሪክ ፍጻሜ፣ ስለ ክርስቶስ፣ የክርስቶስ መስቀል ብቸኛ የመዳን ምልክት እና የድህነት ሥፍራ መሆኑ የሚመሰክር፣ የእምነት ሰማዕትነት ምን ማለት መሆኑ በጥልቀት የሚያስረዳ ነው። ቅዱስ አባታችን የመላውን የዓለም ሕዝብ ስቃይ ከመላው ሰው ዘር ጋር በመሆን እንደ ክርስቶስ በመሸከም የክርስቶስ መስቀል የእምነት የተስፋ እና የድህነት ታሪክ መሆኑ በእርሱ የሚያምን እንደሚድን ለመመስከር ይኸው በዚህ ቅዱስ ሥፍራ ይገኛሉ፣ ካሉ በኋላ የማርያም ዘፋጢማ መልእክት የተስፋ የሚያምን ድል እንደሚቀዳጅ፣ የሚያበስር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.