2010-05-12 14:28:42

ብፁዕ አቡነ ማምበርት፣ የእምነት ማኅበራዊ፣ ይፋዊ አድማስ


በቅድስት መንበር ወደ በካናዳ መንግሥት መካከል በልኡካን ደረጃ የጋራ ግኑኝነት የጀመሩበት 40 ኛ ዓመት ምክንያት በቅድስት መንበር የካናዳ ልኡከ መንግሥት ክብርት አን ለህይ እምነት በካናዳ ሕዝባዊ መድረክ በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 በጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ምርምር ተቋም ሕንጻ እንዲካሄድ ባዘጋጁት ዓወደ ጥናት፣ የቅድስት መንበርን የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የእምነት ማኅበራዊ እና ይፋዊ አድማስ ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም የሚበጅ እድል ነው በማለት፣ የማያይምኑምት ጭምር የዚህ አድማስ አጠቃሚ የሚያደርግ እንጂ የሚያገል አለ መሆኑ በማበከር የእምነት ማኅበራዊው እና ይፋዊ ገጽታው በጥልቀት አብራርተዋል።

በቪየና ውሳኔ የሚታወቀው እ.ኤ.አ. በ1989 ዓ.ም. የጸደቀው ሰነድ እና የሊስቦናው ውሳኔ ሃይማኖት በማኅበራዊ ጉዳይ ያለው አወንታዊ አስተዋጽኦ ይፋው እውቀና በመሰጠት ያረጋገጠ መሆኑ በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅት ማመን እና አለ ማመን እሴቶች እና የጸረ እሴቶች አመለካከት በእኩል ደረጃ የሚያስቀምጥ እየተስፋፋ ያለው ተዛማጅ ባህል የሃይማኖት ማኅበራዊው አድማሱን የሚቀናቀን ስነ አመለካከት እያሰራጨ መሆኑ በመጥቀስ፣ እምነት ወይም ሃይማኖት የግል ጉዳይ ነው የሚለው አስተሳስብ፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በሚደረገው የጋራው ውይይት እና ግኑኝነት አማካኝነት መሠረት የሌለው መሆኑ ሰፊ የጋራ ማብራሪያ እንደተሰጠበትም ዘክረው፣ ቅድስት መንበር በሁሉም መድረክ በዓለማችን የሃይማኖት ነጻነት እንዲረጋገጥ ከማሳሰብ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚያጠቃልለው ሀሳብ መሆኑም በማስረዳት፣ ለሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መከበር ጥሪ ከማቅረብ እንደማትቆጠብ አስታውሰው፣ በተለያዩ መድረግ በመገኘት እየተስፋፋ ያለው ጸረ ክርስትያን አመለካከት እንዲወገድ አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት የሃይማኖች ነጻነት ይከበር ዘንድ ጥሪ በማቅረቡ ደረጃ ቀዳሚውን ሥፍራ ይዛ እንደምትገኝም አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.