2010-05-12 17:57:17

ሐዋርያዊ ጉብኝት ርሊጳ በነዲክቶስ በፖርቱጋል እየቀጠለ ነው፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ትናንትና በፖርቱጋል ላይ የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዛሬም ቀጥሎ ውለዋል ።

ቅድስነታቸው ፓርቱጋል ርእሰ ከተማ ሊዝቦን የገቡት ትናትና ከቀትር በፊት እንደሆነ የሚታወስ ነው። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ሊዝቦን አውሮፕላን ማረፍያ ሲገቡ የሀገሪቱ የቤተክርስትያን እና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸውል።

የፖርቱጋል ርእሰ ብሔር አኒባል ሲልቫ ከባለቤታቸው እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሊዝቦን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኾሰ ዳ ክሩጽ ፖሊካርፖ በፖርቱጋል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እና ሌሎች የሀገሪቱ ቤተክርስትያን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ቅድስነታቸውን ደማቅ እና ወንድማዊ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ያታወቃል።

በየቅድስት መንበር መገናኛ ብዙኀን መሠረት የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት በገዳመ ፋጥማ የሚያደርጉት ጉብኝት ማእከል ያደረደ ነው።

ይህ በነዲክቶስ በፓርቱጋል እያደረጉት ያሉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሀገራት አቀፍ አስራ አምስተኛ ዑደት መሆኑ የሚታወስ ነው።

አርእሰተ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ እና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በፖርቱጋል ገዳመ ፋጥማ ተሳልመው እና ገብኝተው ነበር ።

ይሁን እና ቅድስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ከቀትር በፊት ሊዝቦን እንደገቡ ሳላሳ ሁለት ሕጻናት ቅድስነታቸውን በመዝሙር እና አበባ ይዘው ደስ የሚያሰኝ አቀባበል አድሮውላቸዋል። የሀገሪቱ ርእሰ ብሔር አኒባል ካቫኮ ሲላቫ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድሮዋል።

ርእሰ ብሔር አኒባል ካቻኮ ሲልቫ ቅድስነትዎ በስሜ እና በፖርቱጋል ህዝብ ስም እንኳን ደህና መጡ በሀገራችን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለህዝባችን እና ሀገራችን ከፍተኛ ምስጢር ያዘለ ነው ማለታቸው ተዘበዋል።

አያይዘውም ከርስዎ ፖርቱጋልን የጐበኙ አርእሰተ ሊቀነ ጳጳሳት ፖርቱጋል የኩላዊት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ታማኝ አጋር ማለታቸው ለማስታወስ እወዳለሑን ያሉት ርእሰ ብሔር ኣአኒባል ኮቻኮ ሲልቫ በቅድስት መንበር እና በፖሩጋል መካከል እኤአ ከ1179 ጀምሮ ጥብቅ ግንኙነት እንዳላቸው ማስታወስ ይቻላል ብለዋል።

በ2004 በቅርቡ በሁለቱ ወገኖች መካከል ስምምነታቸው ማሳደሳቸው እና ማጽደቃቸውም ርእሰ ብሔሩ አስታውሰዋል።

ቅድስነትዎ የሚጐበኝዋት ፖርቱጋል የስዎች ክብር እና መብቶች ጠብቃ በፍትሕ እና ሰላም የምታምን መንግስት እና ሃይማኖት የየፊናቸው ሙያ እየሰሩ ተከባብረው የሚኖርባት ሀገር ናት በማለት ርእሰ ብሔሩ ባሰሙት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ገልጠዋል።

ቅድስነትዎ ፖርቱጋል የክርስትና ምንጭ መሆንዋ እና የክርስትና እሴቶች ጠባቂ መሆንዋ ልገልጽልዎ እወዳለለሁኝ ያሉት ርእሰ ብሄር ፖርቱጋል አኒባል ካቻኮ ሲልቫ አሁን በምንኖርባት በዓለማችን ፍትሕ እና ሰላም በሚጠይቅበት ግዜ እርስዎ የተስፋ እና ሰላም

መልእክት ለዓለማችን ለማዳረስ የሚያደርጉት ጥረት የሚመስገን ነው ካሉ በኃላ እንደገና እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ርእሰ ብሔሩ ንግግራቸውን እንደፈጸሙ ቅድስነታቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ከልብ አመስግነዋል ።

በእግዚአብሔር ጸጋ እና ፈቃድ ልቅዱስ ሐዋርያ መንበር ከተሰየምኩ በኃላ ጥንታዊት እና ውድ የሆነችው ፖርቱጋል ለመጀመርያ ግዜ ለመጐብኝት መቻሌ ከሄሉ ኩሉ እግዚአብርን ምስጋና ይድረሰው ያሉት ቅዱስ አባታን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ገዳመ ፋጥማ ለመሳለም ያስቻለኝ እግዝአብሔር ምስጋናየ ይድረሰው ብለዋል።

ቅድሰነታቸውበአውሮፕላን ማረፍያው ለተቀበልዋቸው የሃይምኖት እና መንግስት ባለስልጣናት ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።

በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ የሚገኙ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከሊዝቦን አውሮፕላን ማረፍያ ተነስተው በክፍት መኪና ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት ተጉዘው ከትንሽ ዕረፍት በኃላ ዶስ ጀረኒሞስ ወደ ተባለ በ1502 የተመሠረተው ገዳም ተጉዘዋል፡ እዚህም ርእሰ ብሔር እና የገዳሙ ሐላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

ቅድስነታቸው ገዳሙ ውስጥ በሚገኝ ቤተ ጸሎት ውስጥ በመግባት ጸልየዋል።

ከዶስ ጀረኒሞስ ገዳም ወደ በለም የርእሰ ብሔር አዳራሽ በመጓዝ የክብር ጉብኝት አድርገዋል በየእንግዶች መዝገብ ስማቸው አስፍረው ፡ ከርእሰ ብሔሩ ተሰናብተው ወደ ሐዋርያዊ ወኪል ቅድስት መበር መኖርያ ቤት ተመልሰው ከሰኙዋቸው ካርዲናልት ጳጳሳት ካህናት እና ጋዜጠኞች ጋር በጋራ በየምሳ ማእድ ተቀምጠዋል።

የፖርቱጋል ሐዋርያዊ መርሃ ዑደታቸው እንዳመለከተው፡ ከጥቂት ዕረፍት በኃላ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በከተማይቱ ሰዓት አቁጣጠር ከቀትር በኃላ ተረሮ ደ ፓኮ ወደ ተባለ አደባባይ ተጉዘው አንድ መቶ ሐምሳ ሺ ህዝብ ተገኘበት መስዋዕተ ቅዳሴ አስርገዋል።

ከሥርዓተ ቅዳሴ በኃላ ወደ መካነ ዕረፍታቸው ቦታ ተመልሰዋል በዚህም የትናትና ሐዋርያዊ ዕለተ ጉብኝት አብቅተዋል







ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዛሬ ጥዋት በከትማይቱ ሰዓት አቆጣጠር ሰባት ሰዓት ተኩል በቦታው በሚገኘው ቤተ ጸሎት በግል መስዋዕተ ቅዳሴ አስርገዋል።

በዘጠኝ ሰዓት ተሩብ በለም ወደ ተባለ የፖርቱጋል የባህል ማእከል ተጉዘዋል። የባህል ማእከሉ እንደ ደረሱ የፖርቶ ከተማ ጳጳስ እና በረኪበ ጳጳሳት የባህል ኮሚስዮን ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኤማኑኤል ክለመንተ እና በሌሎች የባህል እና ኪነ ጥበብ ጠበብት ደማቅ አቀባበል ተደርግላቸዋል። በዚሁ የበለም ማእከል ከአንድ ሺ አምስት መቶ በላይ የባህል እና ሥነ ጽሑፍ ጠበብት ጋር ተገናኝተዋል።

ቅድሰነታቸው ከየባህል ማእከሉ ወደ መካነ ግዝያዊ መኖርያቸው ይኸውም ወደ ኑንጽያቱራ

በፖርቱጋል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል አዳራሽ ተመልሰዋል። ሰዓቱ በሊዝቦን ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን ነው ።

እዚህም የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚስትር ኾሰ ሶቅራጠስ ተቀብለው ማነጋገራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ለመከታተል እዚያው የሚገኙ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኮሰ ሶክራጠስ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በፖርቱጋል የቅድስት መንበር አምባሳደር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሸኝተው ከቅድስነታቸው መገናኘታቸው መገናኛ ብዙኀኑ አስታውቀዋል።

ከግንኘቱ በኃላም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የምሳ እና ዕረፍት ጥቂት ግዜ ካሳለፉ በኃላ ከቀትር በኃላ አስራ ስድስት ሰዓት ተሩብ ወደ ሊዝቦን ሃገራት አቀፍ አውሮፕላን ማሪፈያ ተጉዘዋል ።

ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ ፋጥማ ከተማ ገብተዋል ። እንደሚታወሰው ፋጥማ ከአረብኛ ቋንቋ የተወሰደ ሆኖ ቢሆንም ከተማይቱ ስምንት ሺ ህዝብ የሚኖርባት ብሰሜናዊ ሊዝቦን 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለ።

ፋጥማ ከተማ እኤአ 1971 ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ለሶስት ሕጻናት ይኸውም ለሉቺያ ፍራንቸስኮ እና ጂያቺንታ መገለጽዋ እና ፋጥማ ከተማ ከዚሁ ግልጽት የተሳሰረች መሆንዋ የሚትወስ ነው። መካነ ግልጸቲ ኮቫ ዳ ኢርያ ተብሎ የሚጠራ መካን ገማመ ፋጥማ ተብሎ የሚጠራ በዓመት በሚልዮን የሚቆጠሩ አማንያን የሚጐበኙት ቅዱስ ገዳም ነው።

ግልጸተ ቅድስት ድንግላ ማርያም የሉቺያ ፍራንቸስኮ እና ጂያቺንታ ቅሪቶችም በዚህ ገዳም እንደምገኝ ያወቃል።

ፋጥማ ከተማ የተለዩዩ መንፈሳውያን ማኅበራት የሱባኤ ማእከላት ያከተተ እና የተባረከ መካን መሆኑ አይዘነጋም።

ይሁን እና አሁን ፕሮግራማችን በሚላለፍበት ሰዓት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፋጥማ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ደርሰዋል ።

የፋጥማ ከተማ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ አውጉስቶ ዶሽ ሻንቶስ ማርቶ እና ለሌሎች የቤተክርስትያን ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የከተማይቱ ከንቲባ ቅድነታቸውን ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል ።

የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን ከፋጥማ ከተማ እንዳመልከቱት ፡ ቅድስነታቸው ከእውሮፕላን ማረፍያ በቀጥታ የግልጸተ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተጸሎት አቅንተዋል።

በዚሁ ቤተ ጸሎት በግል ጸልየዋል ። በዚሁ ገዳመ ፋጥማ ሲጠባበቅዋቸው የቆዩት በርካታ ምእምናን እና የቤተክርስትያን አባላት ቅድስነታች አውን በጭብጨባ ተቀብሎዋቸዋል።

በፖርቱጋል የጳጳዊ ኮሚስዮን ፕረሲደንት ብፁዕ ኣአቡነ አንቶንዮ ፋርንሲስኮ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል። ከዚህ ኖሳ ሰንሄሮ ዶ ካርሞ ወደ ተባለ አዳራሽ ተጉዘው በግል ሥርዓተ እራት ፈጽመዋል ። በዚህም የዕለተ ሮቡዕ የዛሬ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ፍጻሜ ሆነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.