2010-05-10 18:11:10

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የንግሥተ ሰማያት ጉባኤ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባቀረቡት የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አስተምህሮ፣ ወደ ፖርቱጋል ነገ የሚጀምሩትን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዲሳካላቸው ምእመናን በጸሎት እንዲሸኝዋቸው አደራ ብለዋል፣ እንዲሁም በብራዚል ለሚካሄደው ሃገራዊ የቅዱስ ቍርባን ኮንግረስም ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።
የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሰረጋቸው በፊት ያቀረቡት ጉባኤ አስተምህሮ እንደሚከተለው ነበር፣ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ግንቦት የሚወደድ ወርና በተለያዩ ነገሮች የሚመረጥ ነው። በመንፈቀ ክበባችን ፀደይ በትለያየ ቀለማች ባላቸው ብዙ አበባዎች አሸብርቆ ይገኛል፣ የአየር ጠባዩ ለሽርሽር አመቺ ነው። በሥርዓተ አምልኮም ይህ ወር ብዙውን ጊዜ ሃሌ ሉያ ብለን የምንዘምረው ዘመነ ትንሣኤን ያጠቃልላል፣ ዘመነ ትንሣኤ ከሙታን ተለይቶ በመንሣትና በፋሲካ እምነት የክርስቶስ ብርሃን የሚገለጥበት እንዲሁም በጰንጠቆስጠ ያኔ በተወለደችው ቤተ ክርስትያን ኃይል ያለበሰ መንፈስ ቅዱስን የምንጠባበቅበት ጊዜ ነው። በባህርያዊዉ የጸደይ ዘመንና በሥርዓተ አምልኮአዊ ዘመነ ትንሣኤ የቤተ ክርስትያን ልማድ ወርኃ ግንቦትን ለማርያም መርቀዋል፣ በእውነቱም ማርያም ከፍጥረት የሚፈካ ከሁሉም የበለጠ አበባ በጊዜ ሙላት የተገለጠች ጽገረዳ ናት፣ ይህም የሆነው ጊዜው በደረሰ ግዜ እግዚአብሔር ልጁን ወደ እርስዋ ልኮ ለዓለም አዲስ ጸደይ በሰጠበት ግዜ ነው። እመቤታችን ማርያም በመጀመርያዋ ቤተ ክርስትያን ምሥረታ ላይ ትሕትና ጠንቃቃ ተካፋይ ነበረች፣ የእመቤታችን ማርያም በሐዋርያት መሀከል መገኘት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ማስታወሻና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ዋስትና በመሆን የመጀመርያዋ ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ማእከል ነበረች።
የዛሬው ወንጌል ከቅዱስ ዮሐንስ ምዕራፍ 14 የተነበበው የእመቤታችን ድንግል ማርያም ትእምርታዊ ትርጉም ያቀርባል፣ ኢየሱስ በወንጌሉ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” ሲል ድንግል ማርያም ማኅደረ ቅድሥት ሥላሴ ሆነች ለማለት ነው። እነኚህ ቃላት በቀጥታ አርድእትን የሚያመለክቱ ቢሆንም ቅሉ ለመጀመርያዋና ፍጽምት ሐዋርያ የሆነችው እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያመለክታሉ። ስለሆነም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከሁሉም አስቀድማና ቀድማ የልጅዋ ቃላትን በሙላት ተቀብላ የጠበቀች ናት። ትሕት አገልጋይና ታዛዥ ነች፣ ለዚህም እግዚአብሔር አብ አፈቀራት ቅድስት ሥላሴም ማኅደርዋ አደረጋት፣ እንዲሁም ኢየሱስ ስለመንፈስ ቅዱስ ሲናገር “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” ያለው እንዴት የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ በሆነው ልብዋ ልጅዋ ያለውንና ያደረገውን ሁሉ ስታሰላስልና በእምነት ስትተረጐም ለነበረች ማርያም አይመለከትም ማለት እንችላለን። በዚህም እመቤታችን ድንግል ማርያም በመጀምርያም ይሁን ከትንሣኤ በኋላ የቤተ ክርስትያን እናትና አርአያ ናት።

ውድ ጓደኞቼ በዚሁ ለእመቤታችን በተሰጠው ወር መሀከል እፊታችን ባሉት ቀናት በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት አደርጋለሁ፣ የፖርቱጋል ዋና ከተማ ሊዝቦንና ሁለተኛይቱ ከተማ ፖርቶን እጐበኛለሁ። የጉዞየ ግማሽ ዓላማ የሁለቱ እረኞች ጃሺንታና ፍራቸስኮ የብፅዕና አሥረኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ደብረ ፋጢማን ለመጐበኘት ነው፣ እንደ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በዚሁ የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ምርጥ ቦታ የነበረው የእመቤታችን መካነ ንግደት የምሄደው ለመጀመርያ ጊዜየ ነው ፣ ሁላችሁ በጸሎት እንድትሸኙኝ አደራ እላለሁ፣ በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ ሁላችን ለቤተክርስትያን አማላጅነት በተለይም ለካህናት እንዲሁም ለዓለም ሰላም የእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነትን እንለምን ካሉ በኋላ የንግተ ሰማይ ጸሎትን አሳርገዋል።

ከጸሎቱ በኋላ በብራዚል ለሚከበረው የቅዱስ ቍርባን ኮንግረስ አመልክተው በፖርቱጊዝ ቋንቋ ረዥም ሰላምታ አቅርበዋል፣ በሰላምታውም “እረኞችና ምእመናን ሁላችሁ የብራዚል ልብ በቅዱስ ቍርባን መሆኑን እንድትችሉ ይሁን፣ ኢየሱስ በቅዱሱ ምሥጢረ ቍርባን ከእኛ ጋር ለመኖር በውስጣችን እንዲኖር ራሱን እንዲሰጠን ያለውን ፍላጎት ይገልጻል፣” ሲሉ በዓሉን እንዲጠቀሙበት አደራ በማለት እርሳቸውን ወክሎ በቦታው በሚገኘው ልዑ ካርዲናል ሁመስ ቅርበታቸውና ፍቅራቸውን ገልጸው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.