2010-05-07 15:56:05

ርሊጳበ ወደ ገዳመ ፋጥማ ይጓዛሉ ፡




ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፊታችን ማክሰኛ ግንቦት አስራ ሀንድ ቀን በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደምያደርጉ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል።

ይህ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በፖርቱጋል የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሀገራት አቀፍ አስራ አምስተኛ ሐዋርያዊ መሆኑ ነው ።

በየቫቲካን መገናኛ ብዙኀን ዘገባ መስሠረት ፡ በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በፖርቱጋል የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በገዳመ ፋጢማ የሚያደርጉት ጉብኝተ ማእከል የዳረገ ነው።

የነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ግዜቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ማእከል የደረደ እና ትኩረት የሰጠ እንደነበረ ሁሉ የበነዲቶስ አስራ ስድስተኛም እንዲሁ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን ማእከል ያደረገ መሆኑ መገናኛ ብዙኀኑ ያመልከታሉ ።

ቅድስነታቸው ከአሁን በፊት በተወለዱበት በጀርመን የአልቶቲንግ እና በላቲን አመሪካ በብራዚል አፓረሲዳ በፈረንሳ ሉርደስ ላይ የሚገኙ ገዳማት ቅድስት ድንግለ ማርያም መጐብኘታቸው እና ጸልየው መኖራቸው የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውሰዋል።

የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን እንዳመለክቱት ፡ መስከረም ወር 2007 በአውስትርያ ሐዋርያዊ ዑደት ባካሄዱበት ገዳመ ማሪያ /ጸል በጐበኙበት ግዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች እና በተለይ የሚሰቃዩ ሁሉ ፡ ሕይወት እና ድኅነት እንዲቀዳጁ ቀና ብለው መስቀሉን እንዲመልከቱ ትጋብዛለች ማለታቸው ተያይዞ ተወስተዋል።

በቅድስት ማርያም በኩል ከመድኅን ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት እንደሚቻል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በሚሰጡት ትምህርተ ቤተክርስትያን ደጋግመው ማመልከትያቸውም ተገልጸዋል።

እግዚአብሄር ባለበት ሕይወት ተስፋ እና ሰላም አለ ስለሆነም ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅ ስለሆነች እንለምናት እንማጸናት ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እስዋ የህዝበ ክርስትያን ተስፋ እና እናት መሆንዋ መግለጣቸው የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አመልክተዋል።

ማርያም አእምሮአችን እና ልባችን እንዴት አድርገን ለኀያል መንፈስ ቅዱስ እንደ ምንከፍትለት ታሳየናለች ስለሆነም ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመግኘት እና ነፍሳችን ለማዳን እንልመናት ያሉት ቅድስነታቸው በፖሩጋል ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ከማርያም ፋጡማ ለመገናኘት እንደሚጓጉ አመለከቱ በማለት የቫቲካን የዜና አውታሮች ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.