2010-05-07 15:48:17

ሐዋርያዊ ጉብኝት ጳጳሳት በልጅዩም፡


የበልጅዩም ካቶሊካውያን ጳጳሳት ትናትና ቫቲካን ውስጥቪሲታ አድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት መጀመራቸው ተገልጸዋል።

የቫቲካን መግለጫ እንዳመልከተው ፡ የበልግዩም ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት እስከ ፊታችን ቅዳሜ ይዘልቃል ። ጳጳሳቱ በቫቲካን ቆይታቸው ፓስቶራል እና ማሕበራዊ ርእሰ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት ከየቫቲካን ተቋሞች ባለስልጣኖች ጋር ይወያያሉ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋርም ይገናኛሉ በማለት የቫቲካን ጋዜጣ አስታውቀዋል።

በበልጅዩም የማሊነስ ብሩሰል ሊቀ ጳጳስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ አንድረ ሙትየን ጆሰፍ ለኦናርድ እንደገለጡት የበልጅዩም ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሀገሪቱ ውስጥ በየቤተክህነት አባላት በሕጻናት ላይ የተፈጸሙትን የቅሌት ተግባር የውስጠ ሃይማኖቶች ውይይት በተለይ በልጅዩም ውስጥ ከሚገኙ የኢስላም ማኅበረሰቦች ጋር የሚካሄደው ውይይት ትኩረት ያደረገ ውይይት ይካሄዳል።

ባልፈው ቅርብ ግዜ በበልጂዩም የብሩጅ ከተማ ጳጳስ ከረጂም ግዜ በፊት በሕጻናት ላይ በፈጸሙት ቅሌት ምክንያት በገዛ ፈቃዳቸው ከሐላፊነታቸው መውረዳቸው የሚታወስ ነው።

በልጅዩም የተለያዩ ማኅበረ ሰቦች እና ቋንቋዎች አቀፍ መሆንዋ የሚታወስ ሲሆን ቤተክርስትያን በዚህ አኳያ ችግር እንደሌላት የተለያዩ ማኅበረሶብች ህልውና ሃብት እና ጸጋ መሆኑ የማሊነስ ብሩሰል ሊቀ ጳጳስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ አንድረ ሙትየን ጆሰፍ ለኦናርድ አስገንዝበዋል።

ገቢራዊ ካቶሊካዊነት እየቀነሰ በመሄድ ላይ መሆኑ ያማለከቱ ሊቀ ጳጳሱ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ይህንን ለመጠገን በጥረት ላይ መሆናዋ አመልክተዋል።

በወቅቱ ያለው የሀገሪቱ የፓሊቲካ ሁኔታ በየኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት እየተደናበረ ቢሆንም የሃገሪቱ አንድነት የሚጻረር አለመሆኑም ብፁዕ አቡነ አንድረ ሙትየን ጆሰፍ ለኦናርድ ማስገንዘባቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.