2010-05-05 12:18:12

የኬንያ የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች ጥሪ


በኬንያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት የሚገኙባቸው በጠቅላላ የዚህች አገር አቢያተ ክርስትያን መሪዎች የአገሪቱ መንግሥት ሕገ መንግሥት ለማሻሻል በሚል እቀድ መሠረት ይኸንን መርሃ ግብር የሚፈጽመው ብሔራዊ ጉባኤ እያካሄደው ያለው ሕገ መንግሥት የማሻሻል ጥናት የሕይወት ባህል ማክበር በሚል ርእስ ሥር የአገሪት የምስልምና ሃይማኖት መሪዎች ጭምር የፈረሙበት ሰነድ በማስተላለፍ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ይከበር ዘንድ አሳስብዋል።

የአቢያተ ክርስያን መሪዎች የአገሪቱ የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ካድሂ በመባል የሚታወቀው የምስልምና እምነት ፍርድ ቤት መንግሥታዊ መዋቅር ለበስ ሆኒ እንዲቋቋም ያቀረቡት ጥሪ እና እነዚህ ፍርድ ቤቶች መንግሥታዊ እውቅና እንዲያገኙ የሚደርጉት ጥረት በአገሪቱ ሃይማኖታው ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ተካሂዶ በነበረው ሕዝባዊ ምርጫ ተቀጣጥሎ የነበረው ማኅበራዊ እና ጎሳዊ ግጭት እንደምሳሌ በመጥቀስ በመዘከር እንደሚቃወሙት አስታውቀዋል።

የኬኒያ ሕገ መንግሥት እ.ኤ.አ. በ 1963 ዓ.ም ረቆ ገቢራዊ እንደሆነም የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች በማስታስወስ፣ ምንም’ኳ በተለያዩ ዓመታት የተቀያየሩ መንግሥታት አንዳንድ ሕጎችን ያከሉበት ቢሆንም፣ አሁንም ገቢራዊ መሆኑ በመጥቀስም የሕገ መግንሥት ወቅታዊነት ሕገ መንግሥት ማሻሻል በሚል ዓላማ ግብረ ገብና ስነ ምግባር ማግለል ሕገ መንግሥቱን መቃወም ማለት መሆኑም በማብራራት በሕገ መንግሥቱ ሕይወት ከመጸነስ የሚለው ከመወለድ በሚለው አስተሳሰብ እንዲተካ በማድረግ በአገሪቱ ጽንስ ማስወረድ ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት በመቃወም የኬኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲጠበቅ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.