2010-05-05 12:18:18

የካይሮ አልዛሃር ሼክ እና ኢማም መሐመድ ሰይድ ጣንጣዊ


በግብጽ የካይሮ አልዛሃር ሼክ እና ኢማም መሐመድ ሰይድ ጣንጣዊ በሰማንያ አንድ ዕድምያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ሲሆን፡ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በኩል በግብጽ ለሼክ ሙሐመድ አብድ አል ዓዚዝ ዋሲል የሐዘን ተለግራም መላካቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።



በዚሁ መግለጫ መሠረት ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለሼክ እና ኢማም ሰይድ ጣንጣዊ ቤተሰብ እና ለአልዛሃር ቤተሰብ በየኢማም የጣንጣዊ ሞተ ዕረፍት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጠው ጥናቱ ተመኝቶውላቸዋል።



ቅድስነታቸው ለየግብጽ ሼክ ሙሐመድ አብድ አል ዓዚዝ ዋሲል የላኩት የሐዘን መግለጫ ተለግራም ሟዋቹ ትልቅ የሃይማኖት መሪ ከመሆናቸው ባሻገር በካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እና የኢስላም ሃይማኖት መካከል በርካታ ውይይቶች ያካሄዱ ብልህ እና አስተዋይ መኖራቸው እንደሚያመልከት የቫቲካኑ መግለጫ አመልክተዋል።



በቅድስት መንበር የወስጠ ሃይማኖት ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና በግብጽ የአልዛሃር የሃይማኖት ቀዋሚ ኮሚስዮን መካከል በልብ ድካም በድንገት መሞታቸው የተነገረላቸው ሼክ እና ኢማም መሐመድ ሰይድ ጣንጣዊ መሪነት የውስጠ ሃይማኖት በርካታ ውይይቶች መካሄዳቸው በቫቲካን የውስጠ ሃይማኖት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጂን ሉዊስ ቱራን መግለጻቸው የሚታወስ ነው ።








All the contents on this site are copyrighted ©.