2010-05-05 12:17:42

የኡጋንዳ ካቶሊካውያን ጳጳሳትቪሲታ አድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት-2


በምስራቅ አፍሪቃ የኡጋንዳ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ቫቲካን ላይ ቪሲታ አድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው እና ከነሱ በከፊል ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር መገናኘታቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።



ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአምስት ዓመታት አንድ ግዜ ቫቲካን እንደሚጐበኙ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምሰሶዎች የቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ መቃብሮች እንደሚሳለሙ እና ደግሞ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገናኘት አብያተ ክርስትያናቸው በተመከተ እንደሚወያዩ የማይዘነጋ ነው።



የኡጋንዳ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ሰካማንያ ለፊደስ አገልግሎት ዜና እንደገለጡት ካቶልካዊት ቤተክርስትያን ኡጋንዳ በየግዜው እያደገች ለህዝብዋ ሐዋርያዊ እንክብካቤ በመስጠት ላይ ትገኛለች ።



በሌላ በኩል ኡጋንዳ ላይ ባህላውያን እምነቶች በህዝብ ላይ የሚያሳርፉት ተጽዕኖ ቅዱስ ወንጌል ብህዝቡ ላይ እንዲሰርጽ ማድረግ ቀላል እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ሰካምንያ ለፊደስ አገልግሎት ዜና ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።



ከሳላሳ ሚልዮን የሀገሪቱ ህዝብ በመቶ አርባ አንድ ከቶሊካዊ እምነት እንደሚከተል ይታወቃል።



ይሁን እና የኡጋንዳ ቤተክርስትያን የህዝቡ ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ እንደምትጥር ምህረት በማይሰጠው ኤች አቪ ኤድስ የሚሰቃዩ ዜጎች እንደምትንከባከብ የረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበሩ መግለጣቸው ተመልክተዋል።



በሰሜናዊ ኡጋንዳ ከሃያ ዓመታት በላይ በመንግስት እና ሎርድስ ረሲስተንስ አርሚ በተሰየመው ቡድን መካከል በተካሄደው ጦርነት የተፈናቀለ ህዝብ ለመታደግም ሁነኛ ርምጃ መውሰድዋ ሊቀ መንበሩ አያይዘው መግለጣቸው ተነግረዋል።



ሎርድስ ረሲስተን አርሚ የተባለው ቡድን ከሰሜናዊ ኡጋንዳ እንደተባረረ ወደ ተጐራባች ሀገራት ደቡባዊ ሱዳን በኮንጎ ረፓብሊክ እና መካከለኛው ረፓብሊክ አፍሪቃ ተሽግሮ እዚያም እያወከ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው።



ሎርድስ ረሲስተንስ አርሚ ከሰሜናዊ ኡጋንዳ ቢወጣም የሃያ ዓመታት ውድመት መልሶ ለመገንባት ገንዘብ እና ቀና ፍልጎት እንደሚጠይቅ የኡጋንዳ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.