2010-05-05 12:15:33

የኡጋንዳ ካቶሊካዊያን ጳጳሳትቪሲታ አድ ሊሚና ሐወርያዊ ጉብኝት-3


የኡጋንዳ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት እዚህ ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ሐወርያዊ ጉብኝት ሲያካሄዱ መሰንበታቸው እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር መገናኘትቸው የሚታወስ ነው።



በኡጋንዳ የሊራ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጁሰፐ ፍራንጸሊ የኡጋንዳ ጳጳሳት ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያደረጉት ግንኙነት በተመለከተ መግለጫ መስጠታቸው ተመልክተዋል።



ብፅዕነታቸው እንደገለጡት ፡ የኡጋንዳ ጳጳሳት ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያደረጉት ግንኙነት መልካም እና አናጢ መኖሩ ጠቅሰው ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና ጳጳሳቱ የኡጋንዳ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ እና ሀገሪቱ ነክ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው ተዋያይተዋል።



የኡጋንዳ ጳጳሳት ሀገሪቱ ውስጥ ማለት ኡጋንዳ ውስጥ ያለው ማሕበራዊ ሁኔታ ድክነት እና በሽታ በተለይ ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልል ለሃያ ዓማታት በተካሄደው የርስ በርስ ግጭት ህዝቡ በእጅጉ መዳከሙ ቤተክርስትያን አቅምዋ በሚፈቅደው ህዝቡ ለመታደግ ጥረት እያካሄደች መሆንዋ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መግለጣቸው የሊራ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጁሰፐ ፍራንጸሊ አስታውቀዋል።



ግንኝነቱ ሞራል ሰጪ ጠቃሚ እና መልካም ግንኙነት መኖሮም የሊራ ጳጳስ አስገንዝበዋል።



በዚሁ በስሜናዊ ኡጋንዳ ዓቢይ ኤኮኖምያዊ መልሶ ግንባታ ብቻ ሳይሆን ዳግም ህንጸተ መንፈስ እንደሚያሻ ብፅዕነታቸው አያይዘው ገልጠዋል።



ለሃያ ዓመታት የተገንላታ እና የተሰቃየ የስሜናዊ ኡጋንዳ ህዝብ ሁለ ገባዊ ርዳታ እንደሚያስፈልገው ብፁዕ አቡነ ጆሰፐ ፍራንጸሊ የሊራ ጳጳስ ማብራራታቸው ተመልክተዋል።


በአጠቃላይ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአምስት ዓመት አንድ ግዜ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የጥምረት ምሰሶዎች የሆኑ ቅዱሳን ጰጥሮሰ ወ ጳውሎስ መቃብሮች ለመሳልም እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለመገናኘት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.