2010-05-05 12:17:47

የኡጋንዳ ብፁዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ቪሲታ አድ ሊሚና ሕዋርያዊ ጉብኝት


ባለፉት ቀናት የኡጋንዳ ብፁዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳት እዚህ ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ሕዋርያዊ ጉብኝት ሲያካሄዱ መሰንበታቸው የሚታወስ ሲሆን እነሱ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ እንደጨረሱ ፡ የሱዳን ጳጳሳት በተመሳሳይ ሐዋርያዊ ጉብኝት መጀመራቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።



ከአፍሪቃ ሀገራት ብስፋት በላቀች ሱዳን ከሳልሳ ሰባት ሚልይቶ የሚበልጥ ህዝብ የሚኖርባት በመቶ ሰማንያ የኢስላም ሃይማኖት ተከታይ በመቶ አስራ ሰባት ክርስትያን የሚኖርባት መሆንዋ የሚታወቅ ነው ።



ሱዳን ከአሁን በፊት በደቡብ አሁን በስሜናዊ ምዕራብ እና ምስራቃዊ ግጭት የሚታይባት ሱዳን ፡ፊታችን ሚያዝያ ወር አስራሀንድ ቀን እኤአ ፓርላመንታዊ ህዝባዊ ምርጫ ለማከናወን በዝግጅት ላይ የምትገኝ ከአንድ ዓመት በኃላም የደቡባዊ ሱዳን ህዝብ በረፈረንደም በውሳኔ ህዝብ ከነጻነቱ እና ከሰሜን ሱዳን ሕብረት የሚወስንበት ግዜ መሆኑ የሚታወስ ነው ።



በዚሁ ቪሲታ አድ ሊሚና በመሳተፍ ላይ ያሉ በደቡባዊ ሱዳን የሩምበክ ጳጳስ ብፁዕ ኣአቡነ ቸሳረ ማጾላሪ ፓርላምነታዊ ምርጫው ሰላማዊ ትክክለኛ ነጻ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልጠው ውጤቱም ለሰላም እና እድገት የሚያራምድ ውጤት እንዲሆን ያላቸውን ተስፋ አመልክተዋል።



የሱዳን ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ድሃ እና ከድሆች ጐን ተሰልፋ እንደምትገኝ የገልጹት የሩምበኩ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ሞጾላሪ ብ2005 እኤአ ኬንያ ላይ በደቡባዊ ሱዳን እና ሰሜን ሱዳን የሃያ ዓመታት ጦርነት እንዲገታ ያደረገ የሰላም ስምምነት ዘገምተኛ ይሁን እንጂ የሰላም ተስፋ እንደሚታይበት አስታውቀዋል።



የደቡብ ሱዳን ህዝብ መንነቱ የሚያረጋግጥበት እና ሐላፊነት የሚሸከምበት ግዜ መቀረቡ ያመልከቱት የሩምበክ ጳጳስ ሀገሪቱ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።



በሰሜናዊ ምዕራብ ዳርፉር ላይ ያለው ሁከት አሳሳቢ መሆኑ እና ይህም ሰላማዊ እና ፍትሀዊ መፍትሔ እንድያገኝ የሱዳን ቤተክርስትያን እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች የሚጠብቁት ጉዳይ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቸሳረ አስገንዝበዋል።



የሱዳን ብጽዓን ጳጳሳት በቅርቡ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እንደሚገናኙ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.