2010-05-05 12:17:56

በሰሜናዊ ናይጀርያ ጆስ ላይ ባለፉት ቀናት የተከስተው ግጭት የአምስት መቶ ሰዎች ሕይወት መቅጠፉ እየተነገረ ነው ።


ሁከቱ እና ግጭቱ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ጐሳዊ ግጭት መሆኑ እየተምለክተ ነው ።



የናጀርያ መንግስት ዘግይቶም ቢሆን በርካታ ወታደሮች ወደ ጆስ መላኩ ተገልጸዋል።





ሃይማኖታዊ ይሁን ጐሳዊ በርካታ ሰዎች በሕይወታቸው የተቃጠሉበት አዘግናኝት ድርጊት መኖሩ ያመልከተ ዜና እንዲህ ዓይነቱ አራዊታዊ ያለው ድርጊት በሀያ አንደኛ ሚእተ ዓመት መፈጸሙ አሳፋሪ ድርጊት ነው ብሎታል።

የጆስ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢግናጽዩስ ካይጋማ እንደገለጡት ፡ አጥቂዎቹ የኢስላም ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ ተጠቂዎቹ ክርስትያን መሆናቸው በማረጋገጥ ፡ በሁለት ጐሳዎች መካከል ቂም በቀል የታከለበት መጥፎ ግንኙነት እንዳላቸው አስረድተዋል።



ጆስ ማለት በየክልሉ ቋንቃ ሰላም ማለት ቢሆንም ወደ ሲኦል በመቀየር የስዎች ሕይውት ከንቱ የሚጠፋባት እየሆነች መምጣትዋ ብፅዕነትቸው አመልክተዋል።



በየናይጀርያ መንግስት ፕረሲዳንት አድዋ ከአቡጃ የተላከ የመንግስት ልዑካን ብድን ሁኔታው እያጣራ መሆኑ ያመልከቱት ብፁዕ አቡነ ኢግናጽዩስ ካይጋማ እሳቸውም ከልዑካን በድኑ ጋር ተገናኝተው የጥቃቱ መንስኤ እና መፍትሔው ትኩረት የሰጠ ውይይት ማካሄዳቸው አስታወቅዋል።



ዓለም አቀፍ የኢስላም ጉባኤ የጆስ ሁከት እና ግጭት ይህንን ተከትሎ የተፈጸመ ግድያ ማውገዙ ከአቡጃ የድረሰ ዜና ገልጠዋል።



Human Rights Wach የሰው መብት ተከራካሪ ድርጅት የናይጀርያ መንግስት የሰው እልቂት የፈጸሙ ወንጀለኞች ሕግ ፊት እንድያቀርባቸው ማሳሰቡ ሌላ ከኒውዮርክ የመጣ ዜና አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.