2010-05-05 12:18:07

በሊብያ ሲርተ ላይ የተካሄደው የአረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ


በሊብያ ሲርተ ላይ የተካሄደው የአረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ መጠናቀቁ ከቦታው የደርሰ ዜና አስታውቀዋል።



በዚሁ ዜና መሠረት የአረብ መሪዎች የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው እና እሰራኤል በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም እና በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻ የተያዘቸው አዲስ የይሁዲዎች ሰፈራ አውግዘዋል።



የፍሊስጤም ራስ ገዝ መሪ ፕረሲዳንት ማሕሙድ ዓባስ ከእስውራኤል ጋር በቀጥታን ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማንኛውም ሰለም ነክ ውይይት አይካሄድም በማለት የሰጡትን መግለጫ በሊብያ ሲርተ ላይ የተሰበሰቡ የዓረብ ሀገራት ጉባኤ መግለጫውን መደገፉ ይህ ከሲርተ የመጣ ዜና በተጨማሪ አስታውቀዋል።



የኤውሮጳ ሕብረት ሀገራትም የእስራኤል ድርጊት የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ሂደት የሚያደናቅፍ መሆኑ በማመመን ድርጊቱን እንዳልደገፉ እዚህ ሮም ውስጥ ተወስተዋል ።



የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን እስራኤል የምታካሄደው ሰፈራ ለሁከት መንስኤ ይሆናል የሚል ግምት መቀስቀሱ ጠቅሰው በሁለቱ ወገኖች ውይይት መቋረጥ የለበትም ሲሉ መግለጣቸው ተመልክተዋል።



ሐማስ የፍሊስጤም ድርጅት አባላት ሮኬት ወደ እስራኤል መወርወራቸው እና እስራኤል አጠፋውን ለመመለስ መዛትዋ ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጠዋል።



አሁንም ይሁን ዘይግቶ በጋዛ የሐማስ አስተዳደር መገርሰስ አለበት ሲሉ የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስተር ስታይንኒትጽ መግለጫ መስጠታቸው ከተልአቪቭ ተነግረዋል።



የእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር በንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል የፍልስጤሞች ጥቃት እንደምትከላከል በሲርተ ከተካሄደው የዓረብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ለክልሉ ሰላም ጠቃሚ ውጤት ይገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ዜናው አክሎ አመልክተዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.