2010-05-04 18:39:19

ርሊጳ በነዲክቶስ በቶሪኖ :


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በሰሚናዊ ጣልያን ቶሪኖ ላይ በሚገኘው ካተፍራል ውስጥ የሚገኘውን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መግነዝ መመልከታቸው እና መጸለያቸው ተመልክተዋል።

ቅስነታቸው ከተማይቱ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ቶሪኖ ሲገቡ ግዜ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የቶሪኖ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሰቨሪኖ ፖለቶ እንዲሁም የከተማይቱ ከንቲባ ሰርጅዮ ኪያምፓሪኖ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርጎዋል ።

ብፁዕ ካርዲናል ሰቨሪኖ ፖለቲ እንደገለጹት ፡ የቅዱስ ጰጥሮስ ሐዋርያ መንበር ተኪ ሀገረ ስብከታችን ለመጐብኝተ በመሀከላችን በመገኘትዎ የሚሰማን ደስታ ከፍተኛ ነው ።

የቤተክርስትያን ልጆች እንደ መሆናችን መጠን የቤተክርስትያኒቱ መንፈሳዊ መሪ ከልብ እንወዳለን ለሐዋርያዊ መሪነትዎ ኅይል እና ጤና እንዲሰጥዎ ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምናለን ።

ብፁዕ ካርዲናል ሰቨሪኖ ፖለቶ አያይዘው ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ ዓቢይ የእምነት መሪ እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አፍቃሪ ነዎት የቶሪኖ ምእመናን እና ቅዱስ መግነዙ ለመጐብነት በመሀከላችን በመገኘትዎ በሀገረ ስብከቱ ስም አመሰግንዎታለሁኝ ብለዋል።

የቶሪኖ ከተማ ከንቲባ ሲኞር ሰርጅዮ ኪያምፓንቲ በበኩላቸው፡ አማንያን እን ኣ ኢ አማንያን እዚህ ከተማችን ውስጥ በሚገኘው ካተድራል የታቀበውን ቅዱስ መግነዝ ጥልቅ ምስጢር በመስተንተን ላይ በሚገኙበት ግዜ ስንቀበልዎ ሚሰማን ደስታ ወሰን የለውም ማለታቸው ተዘግበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቅዱስ መግነዙ በታቀበበት ካተድራል ውስጥ ከጸለዩ በኃላ እንዳመልከቱት ክፉ ነገራት ለመግታት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ገደብ አልባ ፍቅር ማዘውተር ያሻል ብለዋል።

ቶሪኖ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ካርሎ አደባባይ ከሃምሳ ሺ የሚበልጥ ህዝብ በተገኘበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ከቀትር በኃላም ወደ አደባባዩ ተመልሰው ብብዙ ሺዎች ከሚቆጠሩ ወጣቶች ጋር ተገናኝተዋል።

በዚሁ አደባባይ ለተገኙ በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ማሕበራዊ ችግሮች በማንሳት የስራ እጦት አስከፊነት ትኩረት ሰጥተው ወጣቶች ተስፋ እንዳይቆርጡ መክረዋል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቶሪኖ ላይ ኮቶለኞ በተባለ ቦታ በቅዱስ ጁሰፐ ኮቶ ለኞ በተመሰረተው ቤተ ጸሎት የሚገኘው የሕሙማን ቤት ገብኝየዋል

ከሕሙማኑ ጋር ተገናኝተው በጋራ ጸልየዋል ሕሙማኑም አነጋግረዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቶሪኖ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠቃልለው አምሻቸው ውደ ሐውርያዊ መንበራቸው ወደ ቫቲካን ተመልሰዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በቶሪኖ ካተድራል ለትዕይንተ ህዝብ የቀረበው ቅዱስ መግነዝ ክወስጥ ሀገር እና ከውጭ በየዕለቱ በብዙ ሺ የሚገመት ህዝብ እየተመለከተው መሆኑ እና ከሁለት ሚልዮን የመበልጥ ህዝብ ቅዱስ መገንዙ እንዲመለከተው እንደሚጠበቅ ተያይዞ ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.