2010-04-27 18:10:53

ርእሰ ሊቃነ በቅድስት መንበር የተመደቡ አዲስ የበልጂዩም የሲመት ደብዳቤ ተቀበሉ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በቅድስት መንበር የመተደቡት የበልጅዩም አዲስ አምባሳደር የሲመት ደብዳቤ ተቀብለው አምባሳደሩ ማነገጋገራቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ መሠረት ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አምባሳደሩ ተቀብለው በነጋገሩበት ግዜ ፡ ሕይወት እና ክብር ሰው ተኪ የሌላቸው ውድ ርእሰ ጉዳዮች ናቸው በማለት ገልጸዋል።

ቤተክርስትያን የሰው ነጻነት እና ክብር የተጠበቀ እንዲሆን መልእክት ታስተላልፋለች ለዚህም ትቆማለች የሰው ልጅ ህሊናው እንዲመረመርም ትጠይቃለች በማለት ቅድስነታቸው በቅድስት መንበር ለተመደቡ አዲስ የበልጅዩም አምባሳደር ቻርለስ ጊስላይን መግለጥቸው መግለጫው አመልክተዋል።

አያይዘው ባለፈው ቅርብ ግዜ የቅድስና ሥርዓት የተፈጸመላቸው የበልጅዩም ዜጋ ጆሰፍ ደ ፎይስተር አስታውሰው የቅድሱ ክርስትያናዊ ሕይወት እና ፍቅር የሀገሪቱ ክስርትያናዊ እሴት ያመለክታል በማለት መግለጣቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ ገለጸዋል።

ፊታችን ወራ ግንቦት ሶስት ቀን እኤአ የበልጅዩም ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ርእሰ ሊቃነ ጳፕሳት በነዲክቶስ አስታውሰው የሀገሪቱ ቤተክርስትያን በሕብረ ተሰቡ የምትጫውተው ከፍተኛ ሚና የሚመሰገን መሆኑ መግለጣቸው መግለጫው አስታውቀዋል።

በቅድስት መንበር የተመደቡት የበልጅዩም አዲስ አምባሳደር ቻርለስ ጊስላይን በበኩላቸው በልጅዩም የተለያዩ ብሔር ብሔረ ሰቦች ህዝብ አቀፍ መሆናዋ ጠቅሰው ህዝቡ በሰላም በመከባበር እንደሚኖር እና ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት እና የሃይምኖት መሪዎች ምክር ቤት አንድነቱ ጠብቆ እንደሚገኝ እና በልጅዩም በዚሁ የተለያዩ ብሔሮች አንድነት አኳያ አርአያ መሆንዋ መግለጻቸው ቫቲካን ላይ ይወጣ መግለጫ አስገንዝበዋል።

በበልጅዩም መንግስት እና የሃይማኖት መሪዎች መካከል መልካም ግንኙነት እንዳለ በቅድስት መንብ አር የተመደቡት የበልጅዩም አዲስ አምባሳደረ ቻርለስ ጊስላይን መግለጻቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.