2010-04-26 15:57:13

የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል፣ ርእሰ አንቀጽ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 17 ቀን እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በማልታ ያካሄዱት 14ኛውን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ ሞጎስ የተሞላው የእምነት በዓል የተረጋገጠበት RealAudioMP3 እንደነበር የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ከማልታው ሕዝብ አክብሮት እና ፍቅር ያረጋገጡበት እና የቤተ ክርስትያን ዳግም አዲስ እና ጤናማው መንገድ የተመለከተበት ሁኔታ ነበር ብለዋል።

የማልታ ክርስትያናዊ ባህል የቅዱስ አባታችን ጉብኛት የተዋጣለት እንዲሆን አቢይ ደጋፍ ሆኖ መገኘቱ እና የተደረገላቸው የሞቀው አቀባበል የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ አባታችን ለያንዳንዱ አማኝ ምንኛ ቅርብ መሆናቸው የተመሰከረበትም ነበር። የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የወሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት በደል እና ወንጀል መሠረት በማድረግ የቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ዕደት ለመተንተ ሲራወጡ እና ይኸንን የሚያጎላ አጋጣሚ ይገኝ ይሆን ወይ በማለት ሲጠባበቁ፣ ነገር ግን ቅዱስ አባታችን የወሲብ አመጽ ሰለባ ከሆኑት ጋር አብረው በመጸለይ፣ የሰጡት መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ የመገናኛ ብዙኃን ፍላጎት ሳይሳካ ማሰርረቱ እና እምነት መለወጥ፣ ይቅርታን መጠየቅ በኃጢአት መጸጸትን ያመለከቱትበት ያስተማሩበት የመሰከሩበት ሓዋርያዊ ጉዞ ነበር። የጳውሎስን ዱካ በመከተል የፈጸሙት ሓዋርያዊ ጉዞ በመሆኑም፣ ለማልታ ህዝብ በአዲስ መንፈስ በእምነት ነቅቶ እንዲጓዝ ተስፋን ማነቃቃቱ እና ቤተ ክርስትያን ልጆችዋ በፈጸሙት ኃጢኣት የምትጸጸት እና ይቅርታን የምትጠይቅ መሆንዋ የተመሰከረበት ሐዋርያዊ ጉዞ ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.