2010-04-26 15:58:25

ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን


ትላንትና እሁድ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን ይህ በላቲን ሥርዓት የመልካም እረኛ እረኛ በዓል ከሚከበርበት ዕለተ ጋር በማያያዝ 47ኛው ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን አክብራ ውላለች። ዕለቱ ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት RealAudioMP3 የካህናት የገዳማውያን ምስክርነት ከክርስቶስ ጋር ካላችው ወዳጅነት ቅርብ ጓደኝነት የመነጨ መሆን አለበት በማለት፣ ጥሪ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ቢሆንም፣ ጥሪውን የተቀበሉት አገልጋዮች የሚሰጡት እውነተኛው ምስክርነት ጭምር የሚያሻው የሕይወት ምርጫ ነው። ለጥሪ መበራከት መሠረት እግዚአብሔር ቢሆንም ቅሉ የተጠሩት የሚሰጡት የእውነተኛው እና የሙሉ ምስክርነት ሱታፌ እንደሚያስፈልገውም አስረድተዋል።

የኢጣሊያ ብሔራዊው የጥሪ ጉዳይ የሚከታተለው ማእከል ሊቀ መንበር አባ ዶመኒኮ ዳል ሚሊን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የምንኖርበት የሕይወት ምርጫ የጥሪ ምርጫ መሆን አለበት፣ የምንከተለው የሕይወት ምርጫ ጥሪ መሆኑ ከተረዳን የምንኖርበት ጥሪ አድካሚ እና አስልቺ መስሎ ቢታይም ቅሉ እለት በእለት እያደስን ለመኖር የሚያበቃን ጸጋ ከተቀብልነው ጥሪ እናገኛለን።

የጥሪያችን ማነቃቂያዎች ሰዎች ናችው፣ አንድ ካህን ወይንም ገዳማዊ የሚሰጠው ምስክርነት ለክህነት ለገዳማዊ ጥሪ ቀዳሚ ምክንያት ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ ካህን ወይንም ገዳማዊ ክርስቶስን መከትል ያለው ውበት እና ደስታ መስካሪ መሆን ይጠበቅበታል። መሥዋዕትነት እና ብዙ ነገር ገለል ይቅርብኝ የሚያሻው ቢሆንም፣ እውነተኛው ደስታ ክርስቶስ መሆኑ የሚመሰከርበት ሕይወት ነው። አባ ዳል ሚሊን አክለውም ቅዱስ አባታችን በቃል እና በሕይወት የተሸኝ ምስክርነት ይቀርብ ዘንድ ያቀረቡት ምክር እና በተለይ ደግሞ ከእምነት የመጨ እውነተኛው ምስክንረት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የሰጡት ትምህርት በማስታወስ፣ ካህን የስብአዊ እርዳታ ማኅበር ያንድ ድርጅት ሠራተኛ ማለት አይደለም፣ ካህን ለሚሰጠው መንፈሳዊ እና ሰብአዊ አገልግሎት መሠረት እምነት ነው።

አንዳንድ የቤተ ክርስትያን አባላት በፈጸሙት የወሲብ አመጽ ምክንያት መላ ቤተ ርክስትያን እና ውሉደ ክህነት ሲወቀስ እንሰማለን፣ የተጠሩት ጸጋ ሆነው ለራሳችው እና ሌሎች ቡራኬ እንዲያገኙ እግዚአብሔር የመረጣቸው ናቸው። ስለዚህ ጥሪው በሙላት የማይኖር ከሆነ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል፣ ጥሪ በፈረቃ የሚኖር የሕይወት ምርጫ አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ አገልጋዮች የተወደዱ እና ቅዱሳት ለመሆን ተጠርተናል ይላል። በዚህ በክህነት ዓመት ቅዱስ አባታችን አስተማሪዎች ሳይሆን እውነተኛ መስካርያን እንደሚያስፈልጉ በመደጋገም የሰጡት ምክር እለት በእለት ማስታወስ እንደሚገባን የሚያስገነዝበን ዕለት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.