2010-04-26 15:59:48

ካቶሊክ ቤተ ክርስያን በሰሜን አፍሪቃ


እ.ኤ.አ. ከባለፈው ሚያዝያ 19 ቀን እስከ ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የሰሜን አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በሞሮኮ ርእሰ ከተማ ራባት ስብሰባ ማካሄዱ ይዘከራል። ይህ የተካሄደው ስብሰባ እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. ጥቅምት ወር RealAudioMP3 እዚህ በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳ ሲኖዶስ፣ በማስደገፍ በመካከለኛው ምሥራቅ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መረጋገጥ፣ ሰላም ፍትህ እና እርቅ ለማረጋገጥ ቤተ ክርስትያን ከመንግሥት አካላት ከተለያዩ ማኅበራት ጋር እና ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር የምታካሄደው ግኑኝነት እና ውይይት ርእሰ በማረግ እና በዚህ በሰሜን አፍሪቃ የቤተ ርክስትያን ኅላዌ እና አስተዋጽኦ በተሰኙት ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ማካሄዱ ተገልጠዋል።

ስለ ተካሄደው ስብሰባ በማስመልከት የቱኒዚያ ርእሰ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማሩን ላሃም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ባለፈው ዓመት በቫቲካን ስለ ተካሄደው የአፍሪቃ ብፁዓን ጵጳሳት ሲኖዶስ እና የሲኖዶሱ ጠቅላይ ሰነድ በማስደገፍ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ገልጠው፣ በዚህ ክልል ይኸንን ሰነድ መሠረት ያደረገ ተልእኮ ለመፈጸም፣ እንዲሁም ዘንድሮ ጥቅምት ወር ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው የመከላከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና የስደተኞች ጉዳይ የሃይማኖት ነጻነት እና እምነትን መመስከር በሚሉት ርእሶች ሰፊ ውይይት መካሄዱም ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.