2010-04-26 16:00:47

በዛምቢያ፣ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 13 ቀን እስከ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በዛምቢያ የቤተ ክርስያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ርእስ ያደረገ ጉባኤ እንደሚከናወን ፊደስ በማስታወቅ፣ ካህናት ገዳማውያን ዓለማውያን ምእመናን በጠቅላላ 100 ተጋባያን RealAudioMP3 የሚሳተፉበት የቤተ ርክስትያን ተልእኮ ከባለፈው የአንድ መቶ ዓመት ልምድ በመነሳት እና በአሁኑ ወቅት ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ምን እንደሚመስል የሚዳስስ እንደሚሆን በዛምቢያ የጳጳሳዊ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ተጠሪ ኣባ በርናርድ ማካዳኒ ዙሉ ማስታወቃቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

ባለፈው ዓመት በተካሄደው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በማስደገፍ በዚህች አገር የሚከናወነው የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ምን እንደሚመስል በማጤን፣ በአዲስ መንፈስ ለማነቃቃት እና እያንዳንዱ የቤት ክርስትያን አባል ወንጌላዊ ልኡክ መሆኑ እንዲገነዘብ የሚያነቃቃ ጉባኤ እንደሚሆንም፣ የአባ ማካዳኒ ዙሉ መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

ሕዝበ እግዚአብሔር ወንጌልን ለማስፋፋት መጠራቱ የሚያሳስብ እና ይኸንን ኃላፊነቱን እንዲገነዘብ እና እግብር ላይ እንዲያውለው፣ ምእዳን የሚያገኝበት ስብሰባ እንደሚሆንም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.