2010-04-26 15:56:04

በሥነ አኃዝ የተራቀቀው የመገናኛ ብዙሃን ሰብአዊነት የተሞላው ማድረግ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ቅዳሜ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የጉባኤ አዳራሽ፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሥነ አኃዝ ሥልት በተራቀቀው የመገናኛ ጉዳይ በኵል ስለ ሚቀርበው ምስክርነት RealAudioMP3 ርእሰ ጉዳይ እንዲወያይ በጠራው ዓውደ ጥናት የተሳተፉትን ተቀብለው መሪ ቃል ሰጥተዋል።

በዚህ አጋጣሚም ተጋብእያኑን መርተው እዛው የተገኙት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በተጋብእያኑ ስም ባሰሙት ንግግር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመንበረ ጴጥሮስ የተሾሙበት አምስተኛውን ዓመት ምክንያት ለቅዱስነታቸው ከፍ ያለ ምስጋናን አቅርበዋል።

ቅዱስ አብታችን ባሰሙት መሪ ቃል፣ ድረ ገጽ በጠቅላላ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው የመገናኛ ብዙኃን ገና እግዚአብሔርን ላላወቁት እንዲያውቁት የሚታገዙበት እንዲሆኖን በማሳሰብ፣ በተለይ ደግሞ የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን እግዚአብሔር እንዲታወቅ የሚያግዙ አስፈላጊ ምልክቶች የሚተላለፍበት መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል። ምንም’ኳ በተለያዩ ምክንያቶች እንቅፋት ያጋጠማቸው ቢሆንም ቅሉ ገና በልባቸው የፍጹም እና የእውነት መሻት ፍላጎት ላላቸው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል በማስተላለፍ ወደ ቃሉ የሚምራቸውን መንገድ የሚቀርብበት ይሁን ብለዋል።

በመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ አገልግሎት የሚሰጠው አማኝ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ እና የሰው ልጅ መንፈሳዊው ገጽታውን ችላ እንዳይባል ተገቢ አገልግሎት ማቅረብ ይኖርበታል። ቤተ ክርስትያን ፈጽማ ችላ ልትለው የማይገባት መሠረታዊ ተልእኮዋ እንዲንጸባረቅ እና የሰው ልጅ ሰብአዊው ግኑኝነት እንዳይኮላሽ ድጋፍ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣ ካሉ በኋላ ድረ ገጽ አስፈላጊ ነው፣ ሆኖም ሁሉን በእኵል ደረጃ በማስቀመጥ እና በማስተሳሰር ሁሉም ያው ነው፣ የእሴቶች ደረጃ ብሎ የለም የሚለው የተዛማጅ ባህል እውቀት እና በዚህ የሚመራው ግብረ ገብ በሥነ አቃቂር መንፈስ አማካኝነት እያንዳንዱ በሚሰጠው ትንተና እና አስተያየት መሠረት እውነትን በማሳወቅ፣ በመጨረሻ የሰውን ልጅ ጥልቅ መለያውን ዝቅ እስከ ማድረግ የሚያገፋፋው ባህል ቀርቦ በማጤን የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን የተሟላ መልስ ማቅርብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በፊት ያች በመርከብ የምትመሰለው ቤተ ክርስትያንን የመራ እና ያስተዳዳረው እውነተኛው እና ብርቱ ስሜት መሠረት፣ ዛሬ አለ ፍርሃት የድረ ገጽ ዓለም በሚገባ በማወቅ እና እምነት በተሞላው ልብ ማስተዳዳር ያስፈልጋል ብለዋል። ስለዚህ ይኸን ደግሞ የተራቀቀውን የመገናኛ ብዙኃን ሰብአዊነት የማልበስ ኃላፊነትን እንደሚያመለክት አብራርተዋል።

ቤተ ክርስትያን በአዲሱ የገናኛ ብዙኃን ስልት የማትተማመን እና ለተራቀቀው የሥነ ጥበብ ባህል እና መሣሪያ አለ ስነ አቃቂር የምትመለከት ሳይሆን፣ ቤተ ክርስትያን የአማንያን ማኅበረሰብ ከመሆን በሚገኘው ኃይል መሠረት በሞት ላይ ድል የነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሙላት ምስክርነት የምናቀርብበት መሣሪያ መሆን እንዳለበት በጥልቀት አስረድረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በዚህ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሥነ አኃዝ የተራቀቀው የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ በተመለከተ ስለ ሚሰጠው ምስክርነት ለመወያየት በጠራው አውደ ጥናት ተገኘተው ብሥራተ ወንጌል እና የተራቀቀውን የመገኛ ብዙሃንን በሚል ርእስ ሥር አስተምህሮ ያቀረቡት የቫቲካን ረዲዮ አስተዳዳሪ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ ወንጌል የማብሥሩ ጥሪ ወቅታዊው የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያ ችላ ማለት እንደሌለበት ጠቅሰው፣ በዚህ ዘመን ስላለው እና ስለሚታየው ክርስትያናዊ ምስክርነት በማብራራት፣ የምንኖርበት ወቅታዊው ጊዜ እውነት፣ ግልጽነት እና ታማኝነት የሚያሻው ነው። በሚሥጢር ማቀብ እና ሚዛኑ የጠበቀ ጭምት ገለልተኛነት ክብር የሌለው እየሆነ አወንታዊ ገጽታው ችላ እየተባለ መሆኑ አስረድተው፣ ምንም ነገር መደበቅ የለብንም የምናቀርበው ምስክርነት ቃላችን እና ተግባራችን የሚያገናኝ፣ በቃል እና በሕይወት የተደገፈ መሆን አለበት፣ ስለዚህ አስመሳይነትን እና ወላዋይነት የምንቃወም መሆን አለብን ብለዋል፣

የመገናኛ ብዙኃን ደስታን የሚሰጠው እውነት እና ቅንነት የሚበሠርበት እና አብሣሪያንም በበኵላቸውም ታማኞች መስካሪያን ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኙ እግዚአብሔርን አውቀው የሚያስተዋውቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤተ ክርስትያን ከአማኞች ጋር ብቻ ሳትሆን ከማያምኑት እና ክርስቶስን ገና ካላወቁት ጋር የመወያየት ብቃት ሊኖራት ይገባል ያሉትን ሀሳብ በማስታወስ፣ ይህ ደግሞ ማኅበረ ክርስያን ያለውን ኃላፊነት የሚያነቃቃ ተገቢው እና ቅን ኅብረ ምንጭ እግምት ውስጥ ማስገባት የፍቅር ግዴታ ቢሆንም፣ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳታ ሥልጣናዊ ትምህርት በኩል በቤተ ክርስትያን እውነተኛው ትምህርት የተመራ መሆን አለበት። ስለዚህ ኅብረ ብዙ የመገናኛ ብዙኃን ሂደት ለአማኞች ከቤተክርስትያናዊነት መንፈስ የመነጨ ማእከላዊነት እንዲኖረው ያሳስባል፣ ይህ ማእከላዊነት ጣልቃ ገብነት ማለት ሳይሆን ከእምነት እና ከፍቅር የመነጨ ኃላፊነት ነው የሚያመልክተው እንዳሉ ተገልጠዋል።

በዚህ የመገናኛ ብዙኃን እጅግ በተራቀቀብት ዘመን፣ ወንጌልን ማብሠር በሚለው ርእስ ሥር 1300 ተጋባእያን ባሳተፈው ጉባኤ አስተምህሮ ያቀረቡት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የመገናኛ ብዙኃን እና የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ጁሊዮዶሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ የምንኖርበ ዘመን ፈጣን እለተ በእለት እየተለወጠ የሚሄድ ፋታ የማይሰጠው ሥልጣኔ የሚታይበት ነው። ስለዚህ በዚህ ዘመን የሚሰጠው ወንጌላዊ ምስክርነት የእግዚአብሔር ቃል የማስፋፋቱ ተልእኮ ይኸንን እድገት ግምት ውስጥ ያስገባ እና ስልጣኔው ሰውን ማእከል ያደረገ መሆን እንዳለበት የተበከበረት አውደ ጥናት ነበር ብለዋል።

ይህ ባህላውያን የመገናኛ ብዙኃን በሥን አኃዝ እየተራቀቀ የመገናኛ ብዙኃን የመልእክቶች እና የምንጭች መስፋፋት እና እያንዳንዱ በድረ ገጽ በመሳተፍ መልእክት ተቀባይ ብቻ ሳይሆን ምንጭ ጭምር እንዲሆን እያደረገ ባለው አዲስ ሥልት እየተተካ ነው። የተለያዩ የተሌቪዥን የራዲዮ ጣቢያዎች በዚህ የሥነ አኃዝ ሥልጣኔ የመገናኛ ብዙኃን እጅግ እንዲለውጡ እያደረገው ነው፣ በዚህ ኅብረ ምንጭ በተረጋገጠበት ዓለም ቤተ ክርስትያን በተልእኮዋን መሠረት የዚህ መሣሪያ ተገልጋይ መሆን አለባት፣ ቁምስናዎች ሰበካዎች ደረ ገጽ በመሥራት በመንበረ ጴጥሮስ ሥር የወንጌል ቃል አብሣሪያን በመሆን ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ሕንጸት በማቅረብ እውነትን በማበሠሩ ኃላፊነት መሳተፍ ይኖርባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.