2010-04-23 14:37:24

የካቶሊክአቢያተ ክርስትያን ቃለ አቀባዮች ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 26 ቀን እስከ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እዚህ ሮማ መለያ እና የጋራ ውይይት በተሰኘ ርእስ የሚመራ ሰባተኛው የመላ ካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ቃል አቀባዮች ጉባኤ በጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ RealAudioMP3 የመገናኛ ብዙኅን ዘርፍ ያነቃቃው ስብሰባ እንደሚካሄድ ሲገለጥ፣ የስብሰባው ሊቀ መንበር ክቡር ፕሮፈሶር ኾሴ ማሪያ ላ ፖርተ በሰጡት መገልጫ የራስ ክብር ሳይሆን ስብአዊነት ማእከል ያደረገ እና የሰዎችን መልካሙን ነገር የሚያስቀድም ኃላፊነት የሚያጎላ ስብሰባ እንደሚሆን ገልጠው፣ በቅርቡ አንዳንድ ካህናት በፈጸሙት የወሲብ አመጽ የተጠቃቸው ቤተ ክርስትያን እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የራሳቸውን ክብር ለመጠበቅ ሳይሆን የሁሉም ጥቅም በማስቀደም ስለ ጉዳይ የሰጡት መግለጫ እና የአመጹ ሰለባ የሆኑት ዘንድ በመሄድ ያሳዩት ቅርበት አባታዊ ጥበቃ እና የሰጡት ምክር የሚመሰክረው ነው።

በስብሰባው ንግግር በማሰማት የሚሳተፉት የመገናኛ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ፣ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ የቫቲካን ርዲዮ አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ሄለን ዖስማን እንደሚገኙበት ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ። የጀርመን ተወላጅ የቲዮሎጊያ ሊቅ ዡታ ቡርግራፍ በዚህ ከድኅረ ወቅታዊው ሥልጣኔ በሚንጸባረቅበት ዘመን የቤተ ክርስትያን መለያ እንዴት ባለ መልኩ ማቅረብ በሚለው ርእስ ሥር ሰፊ እና ጥልቅ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡም የዜና አገልግሎት በማመልከት በስብሰባው የተለያዩ የዜና አገልግሎት ወኪሎች የሚሳተፉት የክብ ጠረጴዛ ውይይት ያካተተ እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. በማድሪድ ስለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን፣ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በታላቋ ብሪታይን ሊያካሂዱት ተወስኖ ያልው ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ለብፁዕ ካርዲፍናል ጅሆን ኔው ማን ከቤተ ክርስትያን የሚሰጠው ብፅዕና፣ በሮማ በሚገኘው የአይሁድ ሙክራብ ጉብኝታቸው፣ በተመለከተ የመገናኛ ብዙኃን እንዴት ባለ መልኩ እንዳተቱበት እና እያተቱበት መሆኑ በመለየት የቤተ ርክርስትያን ገጽታ በመገናኛ ብዙኃን ዘንድ በሚል ርእስ ሥር ሰፊ አስተምህሮ እና ውይይት ይከናወናል።








All the contents on this site are copyrighted ©.