2010-04-23 14:31:55

ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሰብአዊ እርዳታ ማኅበር


የተለያዩ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የሰብአዊ እርዳታ ማኅበራትን የሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ፣ በአሰላፊነት በሞግዚትነት የአረጋውያን ተንከባካቢ በመሆን በጠቅላላ በቤት ሥራ የሚጠመዱ ስደተኞች ካሉበት RealAudioMP3 ገሚሳዊ የባርነት የኑሮ ሁኔታ ተላቀው፣ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ይረጋገጥላቸው ዘንድ መንግሥታት ኃላፊነት እንዳለባቸው ለማሳሰብ ያቀደ ዘመቻ ማነቃቃቱ ተገልጠዋል።

የዚህ የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ የተራድኦ ማኅበር የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ ማርቲና ላይብሽ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር የነዚህ በቤት ሥራ ተቀጥረው የሚሠሩት ስደተኞች ጉዳይ ቀርቦ በማጤን ዕለታዊ ኑሮአቸው ምን እንደሚመስል ያጠናቀረው ሰነድ እጅግ የሚያሳስብ ነው። አንዲት አገር የምትገለገልበት የሠራተኛ የማስተዳደሪያ ደንብ እያለ እነዚህ በቤት ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩት በእነርሱ እና ባሠሪዎቻቸው መካከል በሚደረገው በጽሑፍ ያልሰፈረ የግል ስምምነት መሠረት የሚከናወን ነው። ስደተኛው ሥራ ስለ ሚያስፈልገው በቀላሉ ለዚህ ዓይነቱ ሕገ የለሽ ሥርዓት እሺ ብሎ ይገዛ ዘንድ ይጋለጣል። ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ስምምነት የሠራተኛ መብት እና ፈቃድ እግምት ውስጥ የማያስገባ ሆኖ፣ የመኖሪያው ፈቃዳቸው ከሥራው ጋር የተያያዘ እየሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ላለ ማጣት ቢከፋቸው ተገዝተው እንዲኖሩ ይገደዳሉ። ይህ ሁኔታ በቀላሉ ለአመጽ ለብዝበዛ አደጋ አጋልጦአቸው ይገኛል። ስለዚህ ይህ የተራድኦ ማኅበር የመኖሪያ ፈቃድ ከሥራው ጋር የተያያዘ መሆን እንደሌለበት እና በቤተ ሠራተኛ እና ባሠሪው መካከል የሚፈጸመው የሥራ የስምምነት ውል የሠራተኛ የማስተዳደሪያ ደንብ መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም የእነዚህ የቤተ ሠራተኞች ጉዳይ የሚከታተል አንድ ሕጋዊ ማኅበር እንዲቋቋም ጥሪ እያቀረበ ነው።

ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ካጠናቀረው የጥናት ዘገባ ለመረዳት እንደሚቻለውም በ 19 አገሮች ብቻ የቤተ ሠራተኞች በሠረተኛ የማስተዳደሪያ ደንብ ሥር የሚተዳደሩ ሲሆን፣ በብዙ አገሮች እነዚህ የቤተ ሠራተኞች የሠራተኛ መብት እና ፈቃድ ተነፍጎአቸው የሚከፈሉት ደመወዝ ባንዲት አገር ካለው ከመደበኛው የኑሮ ደረጃ ጋር የማይመጣጠን እንዳውም እጅግ ዝቀተኛ መሆኑ በማጣራትም መንግሥታት ይኸንን ጉዳይ በመመልከት የነዚህ ሠራተኞች መብት እና ፈቃድ እንዲከበር የማድረግ ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል። ጠቅለል ባለ አነጋገር ዘመቻው ይኸንን እንደሚያመለክት አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.