2010-04-23 14:34:58

አውጽኦተ አጋንንት እና ነጻ የሚያወጣት ጸሎት ጉዳይ


ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም መንበረ ጥበብ በቲዮሎጊያው ክፍለ ትምህርት ዘንድ ስለ አውጽኦተ አጋንንት እና ነጻ የሚያወጣ ጸሎት የጥናት ትምህርት ዘርፍ እንደሚጀመር ሲገለጥ፣ በዚህ የጥናት ዘርፍ ስለ አዳዲስ RealAudioMP3 የሃይማኖት ቡድኖች የሰይጣን አምላክያን የሃይማኖቶ ቡድኖች በተመለከተ ሰፊ እና ጥልቅ ትምህርት የሚቀርብበት መሆኑ ሲገለጥ፣ እምነትን ለማቀብ እና ኅያው ለማድረግ ብሎም ከተሳሳቱ ሃይማኖትች ሕዝበ እግዚአብሔርን ለመጠበቅ ለሚደረገው ግላዊ እና ማኅበራዊ ጥረት የሚደግፍ መሆኑ የአውጽኦተ አጋንንት ጸጋ የተቀበሉ የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር አማካሪ የቲዮሎጊያ ሊቅ ኣባ ጋብሬለ ናኒ ስለ አዲሱ የትምህርት ዘርፍ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ ሰይጣንን ለመገሰጽ እና ለማንበርከክ የሚቻለው በክፋት እና በሞት ላይ ድል በነሳው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ እና በትንሳኤው ጸጋ ነው። ስለዚህ በግል ኃይል የሚገሰጽ የክፋት ኃይል የለም ይህ ጸጋ በቤተ ክርስትያን ዘንድ የሚለይም ነው፣ ማንም ጸጋው አለኝ ብሎ እግብር ላይ የሚያውለው ተልእኮ ሳይሆን ከቤተ ክርስትያን ፈቃድ የሚያስፈልገውም መሆኑ ገልጠው፣ ሰይጣን መንፈስም አካልም ሊሆን ይችላል፣ ይኽ ደግሞ ጌታችን ካስተማረው እርሱም አባታችን ሆይ ከሚለው ጸሎት ለመረዳት እንችላለን፣ ስለዚህ ስነ አእምሮአዊ ፈውስ ሳይሆን ተጨባጭ የሆነው የክፋት አካል የሚያንበረክክ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው።

ሰይጣን የእግዚአብሔር ፍጡር እና የእግዚአብሔር ጠላት ነው፣ ዛሬ በተለያየ የኃጢአት መልክ ተላብሶ ሰዎችን እንደሚያሳድድ አብራርተው፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ሙሉ ነጻነት እውነተኛው ትርጉሙን በማጥፋት እንዳሻኝ ተብሎ በሚኖርበት መንገድ የሚያጋጥም የክፋት መንፈስ ጭምር ነው። ፈውሱ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው ካሉ በኋላ፣ በዚህ በሚጀመረው አዲስ የትምህርት ዘርፍ በስነ ቲዮሎጊያ በስነ መጽሓፍ ቅዱስ የተደገፈ ጥልቅ ትምህርት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.