2010-04-23 14:39:13

ስለ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. የሚቀርብ ጸልተ ታስእት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ ስለ ሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተገነዘበት ቅዱስ ከፈን ፊት የሚያቀርቡት ጸሎት እንዲሁም በዚህ ሓዋርያዊ ጉብኝት በሳቸው RealAudioMP3 ዙሪያ ለሚሰበሰበው ምእመን የውሉደ ክህነት አባላት ማእከል ያደረገ እ.ኤ.አ. ከዛሬ ከሚያዝያ 23 ቀን እስከ ግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጸሎተ ታስእት እንደሚቀርብ ሲር የዜና አገልግሎት የቶሪኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሰቨሪኖ ፖለቶ በመጥቀስ አስታወቀ።

የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት መንፈሳዊው እና ሰብአዊው ክብር ደምቆ እንዲታይ ያለው መልእክት እና ትርጉም በሁሉም ዘንድ እንዲደርስ መጸለይ አስፈላጊ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ ካርድናል ፖለቶ አክለውም፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቃይ ክብደት የሚያጎላው ቅዱስ ከፈን ፊት ቀርበን በመጸለይ የወንድሞቻችን እና የእህቶቻችን ስቃይ እና መከራ እንደ ክርስቶስ ተካፋዮች በመሆን አጽናኙን ክርስቶስ ለመመስከር መጠራታችን የሚያሳስበን ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.