2010-04-23 16:29:04

ርሊጳ በነዲክቶስ የመቁዶንያ አምባሳደር ተቀብለው አነጋገሩ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅድስት መንበር አዲስ አምባሳደር ሆነው የተሰየሙት የመቁዶንያ አምባሳደር ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አመለከቱ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅድስት መንበር አዲስ የመቆዶንያ አምባሳደር የተሰየሙት ጊዮኮ ጊዮርጊየቭስኪ የሲመት ደብዳቤ በተቀበሉበት እና አዲሱ አምባሳደር ባነጋገሩበት ግዜ እንዳመለከቱት ፡ ግብረ ገብነት ያለው ኅብረ ተሰብ ለመገንባት የሀገሪቱ ጥንታዊ ክስርትያናዊ እሴት መጽናት አለበት።

መቀዶንያ የኤውሮጳ ሕብረት ለመሆን የተያዘችው ሂደት ሕጋዊ እና በቅድስት መንበር የተደገፈ መሆኑ በማመልከትም ሀገሪቱ የህዝብዋ ጥንታዊ ክርስትያናዊ ባህል አንግባ የሕብረቱ አባል ትሆን ዘንዳ ያለቸውን ተስፋ መግለጻቸው መገናኛ ብዙኀኑ ገልጸዋል።

መቁዶንያ ላይ ጥንታውያን ሰብአዊ እና ክርስትያናዊ እሴቶች ጉልኅ መሆናቸው በመግለጽም ይህ የሀገሪቱ ህዝብ ማንነት የሚያስረዳ መሆኑ ማመልከታቸው ተገልጸዋል።

የቀድሞ ዩጎስላቪያ መቀዶንያ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን ሰላም አቅባ የተያዘችው የእድገት ጐዳና በመከተል ለፍትሕ ለሰላም እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ትቆም ዘንዳ ቅድስነታቸው በቅድስት መንበር አዲስ የመቆዶንያ አምባሳደር ለተሰየሙት ጊዮርግዮቪስኪ እንደገለጹላቸው ተመልክተዋል።

የተረጋጋ ማኅበራዊ እና ኤኮኖምያዊ እድገት የህዝብ ባህላዊ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ እሴቶች የተጠበቀ መሆን እንደሚገባው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ማመልከታቸው የቫቲካን መገነኛ ብዙኀን አስገንዘበዋል።

በመቁዶንያ እና ቅድስት መንበር መካከል ያለውን ግኝኙነት መልካም መሆኑ ጠቅሰውም የሀገሪቱ ውሁዳን ካቶሊካውያን የእምነት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ ማስታወሳቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.