2010-04-21 13:47:57

ጸሎት ፍቅር የተሞላበት ልባዊ ቅርበት እና ትብብር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ሚያዝያ 16 ቀን 83ኛው ዓመተ ልደታቸውን እንዳከበሩ ሲታወቅ፣ ይኸንን ቀን ምክንያት በማድረግ አሁንም ከጠቅላላው ክፍለ ዓለም የመልካም የልደት ዓመት ምኞት መግለጫ መልእክት RealAudioMP3 እየደረሳቸው መሆኑ ተገልጠዋል።

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ አነሳሽነት በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የልደት እና ለቅዱስ ጴጥሮስ የተመረጡበት 5ኛው ዓመት ምክንያት የአስተንትኖ የመቁጸሪያ እና የመሥዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በሊጉሪያ በሚገኘው በቅዱስ ሎረንዞ ካቴድራል ተገኝተው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እግዚአብሔር ለእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መስጠቱን በማመስገን፣ ከእምነት የመነጨ ፍቅር የተሞላበት ልባዊ ቅርበት እና ትብብር ለቅዱስ አባታችንን በመግለጥ፣ ለሳቸው እና ለሚሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት፣ መሪ ቃል እና አስተዋይነት አድናቆት ካቀረቡ በኋላ አክለውም፣ ብርቱ የእምነተ እና ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስትያን ያላቸው ፍቅር በቃል እና በተግባር መስካሪ መሆቸውም በመግለጥ፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስትያን ዙሪያ ተከስቶ ያለው ችግር እውነትን በመከተል ተገቢ ምላሽ ያገኝ ዘንድ በትህትና በጥበብ በቆራጥነት እና በታማኝነት እያሳዩት ያለው ክትትል እና ጉዳዩን በጥልቀት የመመልከቱ ውሳኔአቸው በማድነቅም መላ ቤተ ክርስትያን ከቅዱስ አባታችን ጎን ነች ብለዋል።

ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ከትላንትና በስትያ ለመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ የተሸሙበት 5 ኛው ዓመት ምክንያት የካርዲናላት ጉባኤ ባቀረቡላቸው የምሳ ግብዣ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ ትወደኛለህን ብሎ ያቀረበለት ጥያቄ የዛሬ አምስት ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ እንዲሆኑ መላው የብፁዓ ካርዲናላት ጉባኤ በመረጣቸው ወቅት ለሳቸው መቅረቡንም በማታስወስ፣ ብፁዓን ካርዲናላት ጉባኤ አባላት እና አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ አቢይ ድጋፍ ሆነው በመገኘታቸውም አመስግነዋል።

በእምነት ወንድሞችህን አጽና የሚለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ በእምነት የማጽናት የጌታችን ኢየሱስ ሞት እና ትንሣሴ ለማበሰር የእግዚአብሔር ፍቅር መስካሪ እንዲሆን ለሰጠው የተልእኮ ኃላፊነት ታማኝ ለመሆን የሚያበቃቸው የትንሳኤ እምነት እንደማይለያቸውም ተስፈኛ መሆናቸው እና የብፅዓን ካርዲናላት ጸሎት ድጋፍ እና ትብብር እንዳይለያቸው አደራ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጠላትህም ይቅር ለማለት የሚያበረታው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅር በማበሠር ላይ እንደሚገኙም የሚታወቅ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.