2010-04-21 13:50:53

የቅዱስ ፒዮ ቅዱስ አጽም የማዛወሩ ሥነ ሥርዓት


ከትላትና በስትያ ከኢጣልያ እና ከኢጣሊያው ውጭ የመጡ በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት መንፈሳዊ የበዓል ሥነ ሥርዓት አማካኝነት የቅዱስ ፒዮ ቅዱሳት ትሩፋት እና አጽም ከነበረበት የቅድስት ማርያም RealAudioMP3 የጸጋ እናት ቅዱስ ሥፍራ በሳቸው ወደ ሚጠራው ቤተ መቅደስ መዛወሩ ተገለጠ። ይህ የቅዱስ ፒዮ ቅዱስ አጽም የማዛወሩ ሥነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለመንበረ ጴጥሮስ የተሸሙበተ አምስተኛው ዓመት በተዘከረበት እለት እና የካፒችን ወድሞች ማኅበር 126ኛው የማኅበሩ ጠቅላይ ጉባኤ ከሚጀመርበት ዕለት ጋር የተያያዘ እንደነበርም ለማወቅ ተችለዋል።

በእንተ ላእለ ቤተ ክርስትያን ቅዱስና የሚታወጅላቸውን ማድነቅ ተገቢ ቢሆንም እምነቱ በማድነቅ ዘንድ የሚታጠር ሳይሆን፣ ቅዱሳን ያሳዩት ተጋድሎ የእምነት ብርታት እና የሕይወት እና የቃል ምስክርነት እያንዳንዱ ክርስትያን የራሱ በማድረግ ክርስያናዊ ጥሪው መኖር እንደሚገባው የሚያሳስብ ሊጡርጊያዊ ሥነ ሥርዓት መሆኑንም በመንፍሳዊ ዑደት የተሳተፉት የካፑቺን ማኅበር አባል ወንድም አንቶኒዮ ቤልፒየደ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ የቅዱስ ፒዮ የሕይወት ታሪክ እግዚአብሔር ወዳጅህን እና በከፋው ድኽነት ጫንቃ ሥር ወድቆ የሚገኙት አፍቅር የሚለውን ወንጌላዊው ጥሪ እንዴት መኖር እንዳለበት የሚያስተምር ነው ብልዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.