2010-04-21 13:49:35

የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መከበር


የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ እ.ኤ.አ. ዛሬ ሚያዚያ 21 ቀን 2010 እዚህ ሮማ በሚገኘው የሮማ ላ ተርዛ መንበረ ጥበብ የስነ ታሪክ ሊቃውነት RealAudioMP3 ስለ ስደተኛ እና ተፈናቃይ ተጓዦች ጉዳይ የሚካሄዱት 30ኛው ዓውደ ጥናት በማስመልከት ከትላትና በስትያን ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ፣ የስደተኞች እና የተጓዞች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በእያንዳንዱ አገር ዘንድ ያለው የስደተኞች የተፈናቃዮች የጥገኞች እና የተጓዦች መመሪያ በቅርብ እንደሚያውቀው በማብራራት፣ በአሁኑ ወቅት በተለይ ደግሞ በኤውሮጳ የድንበር ጸጥታ ዋስትን ለመስጠት በሚል ሰበብ በሃይማኖት በኤኮኖሚ በፖለቲካ በማህበራዊ ምክንያት አገሩን ለቆ የሚሰደደውን ለመቆጣጠር እና ወደ መጣበት ለመሸኘት የሚከተለው አሰራር የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መከበር የሚያዘው የዓለም አቀፍ ውሳኔን የሚጻረር ነው ብለዋል።

በየብስ ጉዞ እና በአየር በረራ አማካኝነት በኩል ወደ ኤውሮጳ አገሮች የሚገባው ስደተኛ የሚያቀርበው የጥገኝንነ ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ ሆኖም ግን እነዚህ ተቀባይነት ያገኙት ከሸሹበት አገር በባህር በር በኩል የሚጎርፈው የሕገ ወጥ ስደተኛ የሚያቀርበው የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት አይሰጡትም፣ ይህ አይነት ምክንያት አልቦ አሰራር ጸረ ስብአዊ መሆኑ በመጥቀስም፣ ማባረር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም አይሆንምም፣ ስለዚህ የማንኛውም አገሮች የሰደተኛ እና የተፈናቃይ መቆጣጠሪያ እና ማስተዳደሪያ ደንብ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ መሠረት የሚያደርግ እና የሚያከብር መሆን አለበት። የኤውሮጳ አገሮችም ይኸንን ዓለም አቀፍ ውሳኔ እና በተጨማሪም በኤውሮጳ ህብረት በኵል የጸደቀው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ጭምር የሚያከበር ሆኖ መገኘት ይኖርበታል በማለት ዛሬ ስለ ተጀመረው ጉባኤ መርሃ ግብር በተመለከተ ከትላትና በስትያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራራታቸው ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.