2010-04-21 13:52:34

ቶጎ፣ 50ኛው የነጻነት ዓመት


ቶጎ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት እጅ ነጻ የወጣችበት 50 ኛው ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ብሔራዊ የነጻነት በዓል እንደሚከበር ሲነገር፣ የአገሪቱ መንግሥት በተለያዩ መግለጫዎች ቀኑ በብሔራዊ እና RealAudioMP3 በክልላዊ ደረጃ ደምቆ እና አሸብርቆ ይከበር ዘንድ ያስተላለፈው ጥሪ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመደገፍም፣ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤት ብሔራዊው የነጻነት ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፣ የአገሪቱ ዜጎች ዕለቱ የጸጋ ዕለት መሆኑ በመገንዘብ፣ ለእዚአብሔር ምሥጋና እና ውዳሴ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል። በአገሪቱ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የነጻነቱን በዓል በተለያዩ ለሶስትስ ቀናት በሚከናወኑት መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች አማካኝነት እንደምታከበረውም ተገልጠዋል። እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የቶጎ ነጻነት እንዲረጋገጥ የደም መስዋዕትነት የከፈሉት የአገሪቱ ልጆች የሚዘከሩበት እና ስለ እነርሱ የሚጸለይበት ዕለት ሲሆን፣ ሚያዝያ 24 በሚያርገው ምሥዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስ ልበ ዘ ንጽህት ድንግል ማርያም የቶጎ ጠባቂ መሆንዋ ዳግም የማረጋገጡ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚከናወንበት ዕለት ሲሆን፣ በዚህ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ፍጻሜም እ.ኤ.አ. ከ 1884 እስከ 1945 ዓ.ም. የሎሜ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ዣን ማሪየ ቸሱ ስለ ድንግል ማርያም የደረሱት ጸሎት ይደገማል። በዚህ የሶስት ቀን መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትም መላው የአገሪቱ ሰበካዎች እና ቁምስናዎች እንደሚሳተፉም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.