2010-04-21 13:31:49

ርሊጳ በነዲክቶስ የብፁዕ ካርዲናል ስፒድሊክ ሥርዓተ ቀብር መርተዋል፡


ባለፈው ዓርብ ከዚህ ዓለም የተለዩ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ የቀብር ሥርዓተ ትናንትና በቅዱስ ጰጥሮስ ካተደራል ተፈጽመዋል ።

በቅድስት መንበር የካርዲናላት ጉባኤ ሊቀ መንባር ብፁዕ ካርዲናል አነጀሎ ሶዳኖ የሥርዓተ ቀብር ቅዳሴ ሲመሩ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የፍትሐቱ ሥርዓት መምራታቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

የቸክ ረፓብሊክ ዜጋ ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ የዘጠና ዓመት አዛውንት መኖራቸው የሚታወስ ነው።

ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ ነጻ እና ከሕጻንናታቸው ጀምራው በልብ ከኢየሱስ ክርስቶስ በወዳጅነት የተሳሰሩ መኖራቸው ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባሰሙት ስብከት ማመልከታቸው መግለጫው አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሥርዓተ ፍትሐት ሥርዓት በፈጸሙበት ግዜ ሟቹ ብፁዕ ካርዲናል ቶምስ ስፒድሊክ የመጨረሻ ቃላት ጠቅስው እንዳመልከቱት፡ ሕይወቴ በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ገጽ ለማየት ጥርያለሁኝ አሁን ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም እሱን ለማየት ስለሚሄድ ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ በመጨረሻ ሕይወታቸው የተናገሩትን ቃል እንደሚያደንቁ እና ዓቢይ መንፈሳዊ እና የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆናቸው ያመለክተናል ማለታቸው ተዘግበዋል።

ዓበይት የእምነት ስዎች በእግዚአብሔር ጸጋ ተውጠው እንደሚኖሩ ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ አርአያ ናቸው ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብፁዕ ካርዲናሉ እና ነፍስሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያሳለፉት ምድራዊ ሕይወት እንደሚመሳሰል መግለጻቸው በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል ሥርዓተ ቀብር ብፁዕ ካርዲናል ስፒድሊክ የተከታተለ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል።

አያይዘው ነፍስሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ሟቹ ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ ወጣቶች እያሉ በምስራቃዊ ኤውሮጳ ሀገራት ሰፍኖ የነበረ ጸረ እምነት የመንግስታት ርእዮተ ዓለም እና በየሃገራቱ አብያተ ክርስያናት ያንሰራፋው ጭቆና እና መከራ ተሻግረው ከክርስቶኣ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው መኖራቸው አስየ የሚያሰኝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ለሁለቱ ዓበይት የኻቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብፁዓን ኣአበው ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ በዕድሜ የገፉ ቢሆንም የመንፈስ ወጣት በመሆን ለቤተክርስትያን ከፍተኛ አገልግሎት መስጠታቸውም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በሥርዓተ ቀብሩ ማስገንዘባቸው ተግለጸዋል።

ስብከታቸው በማያያዝም ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ በብርሃን የተሰኘ ዘለአለማዊ ዕረፍት እና ሕይወት ተቀዳጅተዋል የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በመሆን የማኅበሩ መስራች የቅዱስ ኢግናጽዮስ ዱካ በመከተል ለማኅበሩ ከፍተኛ መንፈሳዊ ውርሻ ትተው ምድራዊ ሕይወታቸው ፈጽመዋል በማለት ማስገንዘባቸው ታውቆዋል።

ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ የብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ ነፍስ ሸኝታ ወደ ክርስቶስ ታደርሰው ዘንዳ እንጸልይ በማለት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ስብከታቸውን መደምደማቸው ተመልክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ብፁዕ ካርዲናሉ ለበርካታ ዓመታት የነበሩበት የኢየሱሳውያን ማኅበር ማእከል ዳይረክተር እሳቸውም ኢየሱሳዊ አባ ማርኮ ኢቫን ሩፕኒክ እንደገለጡት፡

ሟቹ ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ በመንፈስ አባቴ እና የንባበ መለኮት ያስተማሩኝ ሆነው ለሳላሳ ዓመታት ማኅበር ውስጥ አብረን ኖረናል በመንፈሳዊ መሪነታቸው እና አርአያቸው እኔ ብቻ ሳይሆን በርካታ ኢየሱሳውያን መማረከቻው ትዝ ይለኛል ሲሉ ገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ የንባበ መለኮት መጽሐፍ ጽፈው ለንባብ ማብቃታቸው ጠቅሰውም ሐቀኛ የንባበ መለኮት እውቀት ከእግዚአብሔር ጋር እንድተገናኝ ያደርጋል የሚለውን አስተሳሰባቸው ሐቅነቱ ለመመስከር ይቻላል ማለታቸው ከኢየሱሳውያን ማኅበር ማእከል የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

በሕይወታቸው በናዚ ጀርመን እና በኮሚኒስቶስቶች የገጠማቸው እንቅፋት በመንፈሳዊ እምነት ማሸነፋቸው የሚያስታውሱት ጉዳይ መሆኑ ከአንደበታቸው እንደተረዱ የማእከሉ ዳይረክተር ገለጸዋል ።

ዓቢይ መንፈሳዊ አባት ዓቢይ የንባበ መለኮት መምህር ብጹዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ እስከ ምድራዊ ዕረፍታቸው ድረስ በጸሎት እና አስተንትኖ ተጠምደው የነበሩ ለማህበራቸው እና ቤተክርስትያን ከፍተኛ ሐውራይዊ አገልግሎት የሰጡ መሆናቸውም በተጨማሪ ማመልከታቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.