2010-04-20 13:56:00

የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በዚህ ዘመን


በዚህ ሶስት ሺሕኛው ዘመን መባቻ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዴት ባለ መልኩ ገቢራዊ እየሆነ ነው የሚል ሰፊ እና ጥልቅ ርእስ ያደረገ እ.ኤ.አ. በ 1948 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ሥር የጸደቀው ደንብ ክብር እና ፍትህ ለማረጋገጥ ግዴታን ለመወጣት አብቅተዋልን የሚሉት ጥያቄዎች ማእከል ያደረገ ትላትና ፕሮፈሰር የኢጣልያ የሕገ መንግሥት አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት RealAudioMP3 ዳኛ ማሪያ ሪታ ሳውለ እዚህ ሮማ በሚገኘው ላ ሳፒየንዛ በሚጠራው መንበረ ጥበብ መሠረታዊ ትምህርት ማቅረባቸው ተገልጠዋል።

ዳኛ ማሪያ ሪታ ሳውለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአለማችን ከዚህ በፊት የሰብአዊ እና ፖለቲካዊ መብት ለማረጋገጥ የሚለው ውሳኔ አቢይ ትኵረት የተደረገበት መሆኑ በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅት ይላሉ በኤኮኖሚ እና በማህበራዊ መብት ጉዳይ ላይ ትኵረት እየተደረገ ነው። ይህ ደግሞ በኤኮኖሚው ረገድ የእያንዳንዱ ግለ ሰብ እና ማኅበረሰብ ኤኮኖሚያዊ እድገት እና ራስን የመቻሉ መብት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት ያረጋገጠዋል ብለዋል።

የቤተ ርክርስትያን ማህበራዊ ትምህርት፣ በቅርቡ በተባበሩት የአሜሪካ መንግታት ያጸደቀው የሁሉም ዜጎች ጤና ጥበቃ ዋስትና እንዲከበር የሚያዘው መመሪያ የኢንተርኔት ተጠቃሚነት መብት በሁሉም ዘንድ እንዲረጋገጥ፣ ጦርነት ጨርሶ በማስወገድ የሰው ልጅ በሰላም የመኖር መብት እንዲከበር የሚያሳስብ ጥሪ እና ተግባር እንደሚመሰክረውም ገልጠዋል።

በብሔራዊ አቀፍም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ይላሉ፣ የሁሉም ዜጎች መብት እና ፈቃድ እንዲጠበቅ የሴቶች የሕፃናት፣ የአካለ ስንኵላን የስደተኞች የተፈናቃዮች መብት እና ፈቃድ እምንዲጠበቅም ጭምር የሚያሳሰብ የሁሉንም ኃላፊነት ግዴታንም ጭምር የሚያነቃቃ ክንዋኔዎች እየተረጋገጡ ናቸው፣ ከመብት እና ፈቃድ መከበር ውጭ የተገለለ የኅብረትሰብ አባል እንዳይኖር የሚያሳብ ውሳኔ ጭምር እየተረጋገጠ መሆኑ አብራርተው፣ የሁሉም የሰው ዘር ክብር ጥበቃ ለማረጋገጥ በቂ መመሪያ የተወጠነበት ዘመን ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.