2010-04-20 13:57:24

የሰሜን አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ


አልጀሪያ ሞሮኮ ሊቢያ ቱኒዚያ የሰሃራ ሰሜናዊ ክልል አገሮች ያቀፈው የሰሜን አፍሪቃ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በሞሮኮ ርእሰ ከተማ ራባት እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 22 ቀን እስነ ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ስብሰባ እንደሚያካሂድ RealAudioMP3 ፊደስ የዜና አግልግሎት አስታወቀ።

ይህ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስብሰባ በሰሜን አፍሪቃ የሚታየው ልኡካነ ወንጌል የማባረሩ ውሳኔዎች፣ የሐይማኖት ነጻነት መጣስ የሚሉት ርእሶች ሥር የሚወያይ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግልት ከጉባኤው የተሰራጨው መግለጫ በመጥቀስ ሲያስታውቅ፣ በሌላው ረገድ ስብሰባው በዚሁ ክልል ለሚገኙት ስደተኞችን የሚመለከት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እና በዚሁ የአፍሪቃው ክልል በመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመከበር እና ወደ ፍጻሜው በመቃረብ ላይ ያለው የክህነት አመት ጉዳይ ስብሰባው በመምከር፣ በክልሉ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትስያን ከእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተላለፈ መመሪያ መርህ በማድረግ መከናወን እንዳለበትም ውሳኔ የሚያስተላልፍ እንደሚሆን የዜናው አገልግሎቱ ያረጋገጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.