2010-04-20 13:43:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. የማልታው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ምክንያት አብራርተዋል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወደ ማልታ ለሐዋርያዊ ጉብኝት ከመነሳታቸው ቀድመው በአየሮፕላን ውስጥ ለጋዜጠኞች የዚህ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው ምክንያት ሲያስረዱ፣ የአሕዛብ ሐዋርያ የሆነውን የቀዱስ ጳውሎስ ዱካን ለመከተል RealAudioMP3 እና የዚህ ትልቅ ሐዋርያ ማንነት እና መልእክቶቹ የላቀውን ትርጉም ለመመስከር፣ እርሱም ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክት ምዕራፍ 5 ቁጥር 6 ላይ በፍቅር አማካይነት በሥራ ላይ የሚውል እምነት ለመመስከር መሆኑ ገልጠዋል።

የዛሬ 1950 ዓመታት በፊት፣ በማልታው የባህር ክልል ቅዱስ ጳውሎስ ይጓዝባት የነበረቸው መርከብ በተከሰተው ኃይለኛው የባህር መናወጥ አደጋ ምክንያት በማልታ እንዲቆይ እንዳደረገው እና ይኽ ደግሞ በዛች አገር የክርስትናው እምነት እንዲሰበክ ምክንያት መሆኑ አስታውሰው፣ ይኽ አጋጣሚ በአገሪቱ እና ለያንዳንዱ የአገሪቱ ዜጋ እግዚአብሔር ያለውን እቅድ እንዲሰበክ አድርገዋል። ማልታ ክርስቶስን እና በእኛ ኃጢአት እየደመች ያለቸው የእርሱ አካል የሆነቸውን ቤተ ርክስትያንን ታፈቅራለች፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያኑን ያፈቅራል፣ የእርሱ ወንጌልም የሚያነጻ እና የሚፈውስ እውነተኛው ኃይል ነው ብለዋል።

ሁሉም በዚህች በምንኖርባት ምድር ክብሩ ተጠብቆለት ይኖር ዘንድም የሁላችን ኃላፊነት ነው በማለት፣ ከዚህ ጋር በማያያዝ ስደተኞች በሚደርሱበት አገር ይክ ክብር ይረጋገጥላቸውም ዘንድ በማሳሰብ፣ ይኸንን ክርስትያናዊ ባህል ዳግል ለማጉላት ጭምር መሆኑ ማሳወቃቸው የቅድት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.