2010-04-20 13:44:48

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በማልታ የተደረገላቸው አቢይ እና ደማቅ አቀባበል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 17 ቀን እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በማልታ 14ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማከናወናቸውት ሲገለጥ፣ የቅድስት መንበር መግለጫ እንደሚያመለክተውም፣ RealAudioMP3 ቅዱስነታቸው በሉቃ አየር ማረፊያው የአገሪቱ የመንግሥት አበይት አካላት በማልታ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ውሉደ ክህነት እና ሕዝብ ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ፣ ከማልታው ርእሰ ብሔር ጆርጅ አበላ ጋር የተገናኙም ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚም ከርእሰ ብሔሩ እና በብዙ ሺሕ ከሚቆጠሩት ወጣቶች ለቅዱስነታቸው 83ኛው የልደት ዓመት ምክንያት የንኳን የልደት ዓመት መግለጫ ቀርቦላቸዋል።

ቅዱስ አባታችን በሉቃ አየር ማረፊያ ደርሰው፣ ባሰሙት ንግግር፣ ማልታ በኤውሮጳ ለማህበራዊ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ እና ለኤውሮጳ ለቅርቡ ምሥራቅ እና ለሰሜን አፍሪቃ ባህል እድገት አቢይ ሚና መጫወቷንም ጠቅሰው፣ አሁን አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች ነች እንዳሉም ተገልጠዋል።

አገሪቱ ሚሥጢረ ተክሊል፣ ቅዱስ ሚጢር መሆኑ በማክበርና እና ያለው ክብር በማቀብ ረገድ፣ ቤተሰብ የኅብረትሰብ ማእከል መሆኑ እና ህይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲጠበቅ የሃይማኖት ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ በግልም ሆነ በማህበርሰብ ደረጃ የተሟላ እንድገት እንዲረጋገጥ አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ ትገኛለች እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

የማልታ ህዝብ የዛሬ 2 ሺሕ ዓመት በተሰበከው ወንጌል የጸና ባህል ያለው መሆኑም ቅዱስነታቸው በማስታወስ፣ በአገሪቱ የካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ኅልዌ የሰጠው አስተዋጽኦ አቢይ መሆኑ አብራርተው፣ የማልታ መንግሥት ሰብአዊነት ማእከል ባደረገው መርህ መሠረትም ለስደተኞች በጠቅላላ ለአፍሪቃ የሚሰጠው ከክርስትናው ባህል የመነጨው ድጋፍ የሚመሠገን ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም ማልታ ካላት የመልክዓ ምድር አቀማመጥ አንጻርም፣ ለሃይማኖቶች እና ለባህሎች አገናኝ ድልድይ ትሆን እና ከመነጨ ለወንድማማችነት ባህል መረጋገጥ እጆችዋን ትዘረጋ ዘንድ አደራ ብለዋል። በመቀጠል የማልታው ርእሰ ብሔር አበላ ባሰሙት ንግግር፣ የማልታ ባህል ክርስትናዊ ምንጭ ያለው መሆኑ በማብራራት፣ በአሁኑ ወቅት እምነት የግል ጉዳይ ነው የሚለው ዓለማዊ አመለካከት በማረማመድ ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ አስታውሰው፣ ክርስትናዊው ባህል በማንም የሚሻር አይደለም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያረጋግጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.