2010-04-20 13:47:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ያስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት መልስ


የኢጣሊያው ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለ 14ኛው ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት ወደ ማልታ ከመነሳታቸው በፊት የሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዋጣለት እንዲሆን እና መንፈሳዊ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ባህል የሚያነቃቃ እንደሚሆንም በማመን አክለውም፣ ማልታ በመልክዓ ምድር አቀማመጥ ያላት የባህሎች የሃይማኖቶች የሕዝቦች አገናኝ የመሆን RealAudioMP3 ጥሪ የሚያጎላ መሆኑም ጭምር በመጥቀስ በራሳቸው እና በጠቅላላ የኢጣልያው ሕዝብ ስም ባስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት፣ መልካም የሐዋርያዊ ጉብኝት ጉዞ መመኘታቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት መልስ፣ የአሕዛብ ሐዋርያ የሆነው የቅዱስ ጳውሎስ ዱካን በመከተል የሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ጉዞ መሆኑም በመጥቀስ ለኢጣሊያ ሕዝብ ቡራኬአቸውን በማስተላለፍ ሰላም እና ብልጽግናን መመኘታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስተውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.