2010-04-20 13:54:21

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጥሪ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለመንበረ ጴጥሮስ የተሾሙበት አምስተኛው ዓመት ምክንያት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የኢጣሊያ ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን እና ምእመናን ስለ ቅዱስነታቸው እንዲጸልዩ RealAudioMP3 ያስተላለፉት ጥሪ ዛሬ በጠቅላላ በኢጣሊያ ቁምስናዎች መከናወኑ ተረጋገጠ።

ከጠቅላላ የኢጣልያ ሰበካዎች እና ቁምስናዎች ለቅዱስ አባታችን የደስታ መገልጫ መልእክት እየተላለፈ መሆኑም ለማወቅ ሲቻል፣ ቅ.አ..ር.ሊ.ጳ. የዋህ እና መልካም ኢየሱስ በምድር መሆናቸው የተመሰከሩባቸው መልእክቶች መሆናቸውም ተገልጠዋል። በዚህ አጋጣሚም በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት አማካኝነት በተፈጸመው የወሲብ አመጽ የተጠቁትን በመዘከር፣ ይህ ቤተ ክርስትያን እና ሕዝበ እግዚአብሔርን እጅግ ያሳዘነው ኃጢአት በዚህ ወንጀል ስለ ተነኩት ሰበካዎች እና ቁምስናዎች እንዲጸለይ እና እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ልብ እንዲለውጥ እና ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት የንስሐ ጥሪ በሁሉም ዘንድ እንዲፈጸም የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ያቀረቡት ጥሪ ማእከል ያደረገ ቅዳሴ የመቁጸሪያ ጸሎት መቅረቡ ተገልጠዋል።

እነዚህ ያለፉት 5 ዓመታት የቅዱስ አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተልእኮ ያላቸው ከእግዚአብሔር ፍርሃት የመነጨው የላቀው ጥበብ የጎላበት፣ ክርስትና በእግዚአብሔር ቃል የጸና ወንጌል የሚያንጸባርቅ በሊጡጊያ እና በእለታዊ ኑሮ የሚገለጥ እንዲሆን በቃል እና በሕይወት የመሰከሩበት ዓመታት መሆናቸው በቅዱስ ኤጂዲዮ ስም የሚጠራው ተካቶሊክ እንቅስቃሴ መሥራች የታሪክ ሊቅ አንድረያ ሪካርዲ አቨኒረ ከተሰየመው ከኢጣሊያው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ተብራርቶ ይገኛል።
All the contents on this site are copyrighted ©.