2010-04-19 18:30:49

አምስት ዓመት በመንበረ ጴጥሮስ


የዛሬ አምስት ዓምት እ.አ.አ ልክ እንደ ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓም በሮም ሰዓት የምሽቱ 5 ሰዓት ከ50 ደቂቃ አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደተሾሙ የሚያበሥር ነጭ ጭስ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚላካ ጣራ እንደንፁሕ ዕጣን ሲተን ታየ፣ የዘመኑን የማይትክት ሐዋርያ በማጣት ልቡ ተሰልቦ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና በአከባቢው የሚገኙትን ጐዳንዎች ሞልቶ ይጠባበቅ የነበረው ሕዝብ ደስታውን ለመግለጽ ሲያጨበጭብና በሆሆታ ሲዘምር አንድ ሰዓት በማይሞላ ጊዜ 6 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ርእሰ ዲያቆናት ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ኣርቱሮ መዲና “ሃበሙስ ጳጳ” ሲሉ የብፁዓን ካርዲናላት ጉባኤ 264ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ ካርዲናል ዮሴፍ ራጺገርን መምረጣቸው ቅዱስነታቸውም በነዲክቶስ 16ኛ ተብለው እንዲጠሩ መምረጣቸውን አበሥረዋል። ከ5ቀን በኋላ ሚያዝያ 24 ቀን በመሥዋዕተ ቅዳሴ የሽመቱ አክሚምና እረኛ የመሆናቸው ምልክት ቀለቤት በመቀበል የመንበረ ጴጥሮስ ተልእኮን ጀምረዋል።

በእነዚሁ ዓመታት ብዙ ትምህርት ሰጥተዋል የተለያዩ መልእክቶችም ጽፈዋል፣ ስድስት ሓዋርያዊ ሕገጋት ወይም መመሪያዎች ማለትም ኣፖስቶሊክ ኮንስቲቱዩሽን፣ በ2007 ስለ ቅዱስ ቍርባን የሚመለከት ሓዋርያዊ ምዕዳን ማለት ኣፖስቶሊክ አክዞርተይሽን “ሳክራመንቱም ካሪታቲስ” የፍቅር ምሥጢር፣ 3 ዐዋድያን መልእክቶች ወይም ኢንሲክሊካስ ማለት ደዩስ ካሪታስ አስት - እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ስፐ ሳልቪ - በተስፋ ድነናል፣ ካሪታስ ኢን ቨሪታት - ፍቅር በሓቅ ጽፈዋል፣ ለአምስት ዓመታት በእሁድና በዓበይት በዓላት ያስተላለፍዋቸው የመልአክ እግዚአብሔር ወይም የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አስተምህሮዎች፣ በየሳምንቱ የሚሰጡት የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ጉባኤ አስተምህሮ፣ በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ዕለታትን በማስመልከት የሚጽፍዋቸው ልዩ መልእክቶች እንደ ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን፣ ለጾመ አርባ፣ ለመገናኛ ብዙኃን፣ ለወጣቶች ወዘተ። ከዚህም ሌላ በተለያዩ ጊዝያትና ሓዋርያዊ ግኑኝቶች የሚያደርግዋቸው ንግግሮች፣ ለተለያዩ አገራት ብፁዓን ጳጳሳት ሲቀበሉ የሚሰጡት መሪ ቃል፣ የተለያዩ መንግሥታት መሪዎችና ልኡካነ መንግታትን ተቀብለው በሚያነጋግሩበት ጊዜ የሚሰጡት መልእክት ወዘተ፣ እንደ የናዝሬቱ ኢየሱስ የመሰሉ መጻሕፍትም ጽፈዋል።

ሐውጾተ ኖልዎን በተመለከተ በኢጣልያ አገር ውስጥ 17 ሓዋርያዊ ጉብኝቶች አካሂደዋል፣ ከኢጣልያ ውጭ 14 ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ግኑኝቶች ያደረጉ ሲሆን የመጀመርያዊ ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው በትውልድ አገራቸው ጀርመን ከለን ከተማ በተከበረው ዓለም አቀፍ የወጣች ቀን ለመገኘት ነሓሴ 2005 ዓም ሲሆን ጉብኝቱ የተዋጣለት ነበር፣ ትናንት ያጠናቀቁት የሁለት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ለ14ኛ ጊዜ ሆኖ የአምስቱ ዓመት ማገባደጃ ሆኖ ተገኝተዋል፣ እንደ የመጀመርያው ሳይሆን አንዳንድ የቤተ ክርስትያ የውለደ ክህነት አባላት በፈጸምዋቸው የወሲብ ዓመጽና ኃጢኣት ምክንያት የዚሁ ሰለባ ከሆኑት ጋር አብሮ በመጸልይና እንባ የተናነቀበት ውሉዳዊ ማጽጽናት ፈጸሙት።
ዛሬ በቅዱስ ባሲሊካ ለምስጋና ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ከካርዲናላት ጉባኤ አባላት በብዛት በተገኙበት ጳጳሳት ካህናት ደናግልና ምእመናን ተገኝተዋል። የብፁዓን ካርዲናላት ጉባኤ በዚሁ ፈታኝ ጊዜ እጐናቸው መሆናቸውንና ቅርበታቸውን ለመግለጽ የምሳ ግብዣ ኣቅርበውላቸው። የካርዲናላት ጉባኤ ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ሁሉንም ወክለው ንግግር አሰምተዋል፣ ቅዱስነታቸውም የምስጋና ቃላት አቅርበዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.